በትግራይ ክልል 552 ት/ት ቤቶች ዳግም ወደ መማር ማስተማር ተግባር አልተመለሱም ተባለ

0
395

ሐሙስ ግንቦት 3 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) በትግራይ ክልል ከሚያዚያ 24/2015 ጀምሮ የግል እና የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ሥራ መጀመራቸዉን በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ኪሮስ ግዑሽ ተናግረዋል።

ቢሆንም ግን በአሁኑ ወቅት 1 ሺሕ 9 መቶ 40 ትምህርት ቤቶች ትምህርት ቢጀምሩም 5 መቶ 52 የሚሆኑ ት/ት ቤቶች ግን ገና ሥራ እንዳልጀመሩ የቢሮዉ ሀላፊ ገልጸዋል። ለዚህ ምክንያቱ በትምህርት ቤቶቹ የተፈናቃዮች መጠለያ በመሆናቸዉ እንደሆነም ለብስራት ራዲዮ አስረድተዋል።

በተለይም በመቐለ ከተማ ያሉ የግል ትምህርት ቤቶች ትምህርት መጀመራቸዉን የከተማዋ ነዋሪዎች ለራዲዮ ጣቢያው የገለጹ ሲሆን፤ አሁንም ግን የተዘጉ የመንግሥት ትምህርት ተቋማት በከተማዋ እንዳሉ ተናግረዋል።

ተማሪዎች ከሦስት ዓመታት በላይ ከትምህርት የራቁ እና በጦርነት የተፈተኑ እንደመሆናቸዉ ተማሪዎቹ ትምህርት ከመጀመራቸው አስቀድሞ የስነልቦና ድጋፍ ሊደረግላቸዉ እንደሚገባ ነዋሪዎቹ አንስተዋል።

በክልሉ በተለይም በገጠር አካባቢዎች ትምህርት ቤቶች አሁንም የታጣቂዎች ካምፕ መሆናቸዉን ነዋሪዎቹ ጨምረዉ ገልጸዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here