“መዉሊድም ቢሆን እናገለግላችኋለን” ብሎ ያወጣዉ ማስታወቂያ የአገላለጽ ስህተት ነው ሲል የገቢዎች ሚኒስቴር ይቅርታ ጠየቀ

0
437

በገቢዎች ሚኒስቴር ድረ ገጽ ላይ ጥቅምት 29/2012 ግብር ከፋዮችን ከቅጣት ለማዳን “መዉሊድም ቢሆን እናገለግላችኋለን” ብሎ የወጣዉ ማስታወቂያ የአገላለጽ ስህተት ነው ሲል የገቢዎች ሚኒስቴር ይቅርታ ጠየቀ ።

የበዓሉ ቀን መሥሪያ ቤቱ ዝግ እንደነበር በድረ ገጹ ያስታወቀው ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ፤ ነገር ግን በጥቅምት ወር የዓመቱ ትርፍ ግብር መክፈያ የመጨረሻ ወር በመሆኑ ግብር ከፋዮች በወቅቱ ባለመምጣቸዉ በተከሰተ የጊዜ መጣበብ  ምክንያት በመጨረሻዉ ቀንም ከአቅም በላይ ሊሆን ይችላል በሚል የተወሰኑ ሰራተኞች በዕለቱ ገብተዉ ለማገልገል ፈቃደኛ በመሆናቸው እንደሆነ ጠቅሷል።

የገቢዎች ሚኒስቴር በ2012 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት 57.3 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ 102 በመቶ አፈፃፀም ማስመዝገቡ ይታወሳል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here