“የመንግሥት አካላት ዓለማቀፋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸዉ እጠይቃለሁኝ” የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ)

0
735

በኢትዮጵያ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት የዓለም ማህበረሰብ ትኩረት በመሆኑ አገራዊና ዓለማቀፋዊ እርምጃ እንዲወሰዱ ጥሪ አደርጋለሁኝ ብሏል የኢትዮጵያ ህዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ  ዛሬ ባወጣው መግለጫ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔረሰቦች አንዱ የሌላዉ ጠላት አንደሆነ በማስመሰል ላለፋት 28 ዓመታት በህዝብ ላይ የተጫነዉ የዘር ፖለቲካ ዉጤት የሆነዉ ጽንፈኝነት ፡ ዘረኝነት እና ጽንፈኛ ኢትዮጵያዊነትን የፈጠረ ሲል ፖርቲዉ ወቀሳዉን አቅርቧል፡፡

ፖርቲዉ ባለ ዘጠኝ ነጥብ የአቋም መግለጫ የሠጠ ሲሆን የሚፈጸሙ ጥቃቶች ሁሉ ብሄረሰብን ከብሄረሰብ በመለየት እየተፈፀሙ  ያሉ  ስለሆኑ የዓለም አቀፍ ሰብአዊ መብቶችን ጥበቃ አካላት : ከኢትዮጵያ ገለልተኛ አካላት ጋር በጋራ በመቀናጀት እንዲያጣሩት እንዳርጋለን ሲሉ የፖርቲዉ ሊቀመንበር ቆንጂት ብርሃን ተናግረዋል፡፡

የሚፈጸሙ ወንጀሎች ለመከላከል ተገቢዉን ህጋዊ እርምጃ ያልወሰዱ የመንግስት አካላት በኢትዮጵያ ሰብአዊ ጉባኤ፣ በአፍሪካ ህብረት፣ በተባበሩት መንግስታት ሰብአዊ መብት ኮሚሽን እና አዉሮፖ ህብረት ፖርላማ የበኩላቸውን አገራዊና አለማቀፋዊ እርምጃ እንዲወስዱ እንጠይቃለን ብለዋል፡፡

የዘር ጥላቻ የሚያራግቡ የመገናኛ ብዙሃን አዉታሮች የሚጠቀሙ የፖለቲካ ፓርቲዎችና አደረጃጀቶች እንዲታቀቡ አልያም ሊታገዱ ይገባል ብሏል ፓርቲዉ፡፡፡

በመግለጫዉ ፖርቲዉን በሊቀመንበርነት ሲመሩ የቆዩትን አቶ መርሻ ዮሴፍ በአገሪቱ ህግ መሠረት የዉጭ ዜግነት ያላቸዉ በመሆኑና በፖለቲካ እንቅስቃሴ መሳተፍ ስለማያስችላቸዉ መተካታቸዉን አዲስ ማለዳ በፖርቲዉ ጽህፈት ቤት በነበራት ቆይታ አረጋግጣለች፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here