አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ በስድስት ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ

0
645

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ አማኑኤል ሆስፒታል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመው ግለሰብ በስድስት ዓመት ፅኑ እስራት ተፈረደበት። ጌትነት ተስፋየ የተባለው ግለሰብ የግል ተበዳይን ተቀጥራ በምትሰራበት ቤት ውስጥ በመግባት አፏን በማፈን እና በቢላ በማስፈራራት ድርጊቱን መፈፀሙን የዐቃቤ ሕግ መረጃ ያመላክታል።

ተከሳሹም ፍርድ ቤት በመቅረብ ድርጊቱን እንዳፈጸመ ክዶ የተካራከረ ሲሆን ዐቃቤ ሕግ በበኩሉ ደግሞ ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት ልደታ ምድብ ችሎት የሰነድ እና ሰው ምስክሮችን ከተበዳይ የሐኪም ማስረጃ ጋር በማቅረብ ተከራክሯል። በዚህም ሒደት ተከሳሽ ጌትነት ተስፋየ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘታቸው በደረጃ 3 የእስራት እርከን 25 ስር የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸው እንደ ቅጣት ማቅለያ ተይዞላቸው በስድስት ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳ ተላልፏል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here