የኅዳሴው ግድብ የኮርቻ ግድቡ የአርማታ ሙሊት ስራ ተጠናቀቀ

0
1235

 

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኮርቻ ቅርፅ ግድብ ሙሊት ስራ ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁ ታወቀ።

ቀደም ሲል ከ14 ሚሊየን ሜትር ኪዩብ በላይ የድንጋይ ጥቅጥቅ ሙሊት ስራ መከናወኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የታላቁ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ምክትል ስራ አስኪያጅ በላቸው ካሳ ገልጸዋል።

ከኮርቻ ግድቡ ቀሪ ስራዎች መካከል 30 ሳንቲ ሜትር ሙሊት ይፈልግ የነበረው የላይኛው አርማታ ሙሊት (ፌስ ስላብ) ስራ  ሙሉ ለሙሉ መጠናቀቁ  ከህዳሴ ግድብ ስራዎች መካከል አንዱ ወሳኝ ስራ እየተጠናቀቀ መሆኑን ያሳያል ብለዋል።

የኮርቻ ግድቡ 5 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር ርዝመትና 50 ሜትር ቁመት ያለው ሲኖረው በአሁን ሰዓት 97 በመቶ አፈፃፀም ላይ ደረሰ ሲሆን ከዚህ በኋላ ቀሪ የማጠናቀቂያ ስራዎች ብቻ የሚከናወኑለት እንደሚሆንም ገልጸዋል።

በኮርቻ ግድብና በዋናው ግድብ ላይ አተኩሮ ሲሰራ የነበረው የሲቪል ስራ የኮርቻ ግድቡ በመጠናቀቁ ዋናውን ግድብ በፍጥነት ለማጠናቀቅ ተጨማሪ አቅም እንደሚሆን አቶ በላቸው ተናግረዋል።

በቅርቡ  የሦስቱ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሮች በግድቡ ዙሪያ በአሜሪካ እና የዓለም ባንክ አወያይነት በዋሽንግተን ዲሲ ውይይት ካደረጉ በኋላ ባወጡት መግለጫ በግድቡ ወሃ አሞላል እና ግንባታ ዙሪያ እስከ ጥር 6/2012 ድረስ ስምምነት ላይ ለመድረስ የተስማሙ ሲሆን ይህን ማድረግ ካልቻሉ ግን በ2015 (እ.ኤ.አ.) አገራቱ የፈረሙት የመርሆች ስምምነት አንቀፅ 10 ተግባራዊ እንደሚደረግ ቃል መግባታቸዉ ይታወሳል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here