ሜቴክ 41 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በማትረፍ ከልማት ድርጅቶች ቀዳሚ ተርታ ላይ ተቀመጠ

0
551

በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የመንግሥት የልማት ድርጀት ሆነው በአምራች ዘርፍ ከተሰማሩት አምስት ድርጅቶች ውስጥ ኢንጅነሪንግ እና ብረታ ብረት ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) 41 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በማትረፍ በኹለተኛ ደረጃ ላይ ተቀመጠ።

ሪፖርተር ጋዜጣ እንደዘገበው የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ በሥሩ ከሚያስተዳድራቸው እና በአምራች ዘርፍ የተሰማሩ አምስቱ ድርጅቶች በሩብ ዓመቱ በድምር 174 ሚሊዮን ብር ያስመዘገቡ ሲሆን ሜቴክ 41 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ትርፍ በማስመዝገብ ከብሔራዊ አረቄ እና አልኮል ፋብሪካ በመቀጠል ኹለተኛ ሆኗል። ሜቴክን በመከተልም ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት፣ ኮሚካል እና ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን እና ኢትዮጵያ ፐልፕና ወረከት አክሲዮን ማኅበር በቅደም ተከተል ተቀምጠዋል።

ሜቴክ በባለፈው ዓመት ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ኪሳራ አስመዝግቦ እንደነበር ዘገባው አትቷል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here