ዶ/ር አምባቸው መኮንን የተሰውበት 4ኛ ዓመት የመታሰቢያ መርሀ ግብር ተካሔደ

0
554

ሐሙስ ሰኔ 15 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የቀድሞ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር አምባቸው መኮንን እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የተሰውበት 4ኛ ዓመት የመታሰቢያ መርሀ ግብር በዛሬው ዕለት ተካሂዷል፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ አዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤን ጨምሮ የፌደራል እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ ቤተሰቦቻቸው እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይም የዶ/ር አምባቸው ልጅ መዓዛ አምባቸው ባደረጉት ንግግር፤ ዶ/ር አምባቸው የተሰዉለት አላማ ከግብ እንዲደርስ እና የአገሪቱን ልማት ለማስቀጠል በአባታቸው ሥም ፋውዴሽን መቋቋሙን ተናግረዋል።የቀድሞው የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር አምባቸው መኮንን ሰኔ 15/2011 በሕዝብ ሥራ ላይ እያሉ መሰዋታቸው ይታወሳል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here