ለ70 ዓመታት በሥራ ላይ የነበረው የፌደራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ክፍያ ሕግ እየተሻሻለ መሆኑ ተገለጸ

0
395

አርብ ሰኔ 16 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) ስድስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በትናንትናው ዕለት ባካሄድው 2ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 25ኛ መደበኛ ጉባኤ፤ የፌደራል ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ክፍያን ለመወሰን በቀረበው ረቂቅ ደንብ ላይ ውይይት ያካሄደ ሲሆን፣ በረቂቅ ደንቡ ላይ የቀረቡ ሀሳቦችን ጨምሮ ለዝርዝር ጉዳዮች ለሕግና ፍትህ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል።

ከ1945 ጀምሮ በሥራ ላይ ያለው ሕግ፣ ምንም ዓይነት ማሻሻያ ሳይደረግበት እስካሁን መቆዩቱ በዳኝነት ዘርፉ የሚሰሩ ሥራዎች ወጤታማነት ላይ ጥያቄ እያስነሳ በመሆኑ ደንቡን ማሻሻል አስፈላጊ ሆኗል ነው የተባለው።

እንዲሁም ፍርድ ቤቶች ቀልጣፋና ፍትሃዊ አግልግሎት መስጠት ያስችላቸው ዘንድ ብሎም አሁን ካለው የሕዝብ ቁጥር፣ የቴክኖሎጂ እድገትና ሌሎች ነባራዊ ሁኔታዎች አንጻር፤ የዳኝነት አገልግሎት አሰጣጥን ውስብስብነት ባህሪና ይዘት ያገናዘብ የክፍያ ተመንና ስርዓት እንዲኖር ለማድረግ ደንቡ እየተሻሻለ መሆኑ ተጠቅሷል።

ረቂቅ ደንቡ ጠቅላላ ድንጋጌዎችን ጨምሮ በአራት ክፍሎች እና በ25 አንቀጾች የተደራጀ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ የዳኝነት ክፍያ አከፋፈልን፣ በዳኝነት ክፍያ መጠን ላይ የሚፈጠር አለመግባባት ስለሚፈታበት ሂደትን እንዲሁም ለዳኝነት የተከፈለ ገንዘብ ተመላሽ ስለሚደረግበት ሁኔታ እና ሌሎች ድንጋጌዎችን የያዘ እንደሆነ ተመላክቷል።

ሆኖም ዜጎች መብትና ጥቅማቸው በተነካ ጊዜ ጉዳያቸውን ወደ ፍርድ ቤት ማቅረብ የማይታለፍ መብታቸው በመሆኑ፤ በክፍያ ምክንያት መብታቸው ሲገፋ ጉዳያቸውን ወደ ፍርድ ቤት ሳያቀርቡ እንዳይቀሩ በማሻሻያው ላይ ከፍተኛ ጥንቃቄ መደረግ እንዳለበት የምክር ቤቱ አባላት አሳስበዋል።

የክፍያ ስርዓቱ ሲሻሻል በተለይም ሴቶችና የመክፈል አቅም የሌላቸው ዜጎች በገንዘብ ምክንያት የዳኝነት አገልግሎት ሳያገኙ እንዳይቀር ቋሚ ኮሚቴው በትኩረት ሊመለከተው እንደሚገባም ተጠይቋል።

ፍርድ ቤቶች ለሚሰጡት የዳኝነት አገልግሎት ፍትሃዊና ተመጣጣኝ የዳኝነት ክፍያ ማስከፈል እንዳለባቸው በሥራ ላይ ያለው የ1958ቱ የፍትሃ ብሄር ሥነ ስርዓት ሕግ ይደነግጋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here