በድሬደዋ ከተማ በድጋሚ ግጭት ተቀሰቀሰ

0
512

በድሬደዋ ከተማ እንደገና ግጭት በመቀስቀሱ ምክንያት ህዳር 2/2012 ለሊት ተኩስ እንደነበር የአዲስ ማለዳ ምንጮች ገልጸዋል።በተለይም በቀፊራ እና ገንደሐራ አከባቢዎች ላይ ከፍተኛ ተኩስ መሰማቱንም ተናግረዋል። በዩንቨርሲቲዉ ዉስጥ ከትላንት ጀምሮ በተቀሰቀሰ ግጭት ከግቢው መውጣት እንዳልቻሉ ተማሪዎች የገለጹ ሲሆን የግጭቱ መነሻ ጥቅምት 29/2012 በወልዲያ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በተከሰተው ግጭት እና በጠፋው የሰው ህይወት ምክንያት በተነሳዉ ግጭት መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል ።

ምንጮች ጨምረው እንደገለፁት በቀፊራ እና ገንደሐራ በተባሉ የከተማዋ አካባቢዎች ሌሊቱን ሙሉ ተኩስ ሲሰማ ከማደሩም በተጨማሪ ጥዋትም መቀጠሉን እና የተጎዱ ሰዎች ቢኖሩም ቁጥራቸው በውል እንደማይታወቅ ተናግረዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ በተቀሰቀው አለመረጋጋት ተማሪዎች ወደ ውጪ መውጣት እንዳይችሉ መውጫ በሮች ዝግ እንደሆኑና ከዩኒቨርስቲ ውጪ ለሚመገቡ ተማሪዎች ፈታኝ እንደሆነ የአዲስ ማለዳ ምንጮች ከድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ተናግረዋል።

ከዚህ በፊት በከተማዋ ተከስቶ በነበረው ግጭት ምክንያት  የበርካታ ሰዎችን ሕይወት በመቅጠፍ እና በንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት ማድረሱ ይታወሳል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here