የአንበጣ ወረራ ሊስፋፋ እንደሚችል ተጠቆመ

0
318

ለባለፉት ኹለት ወራት በኢትዮጵያ የተከሰተው የአንበጣ ወረራ ሊስፋፋ እንደሚችል የምግብ እና ግብርና ድርጅት አስጠነቀቀ። በየመን እና ሶማሊ ላንድ በድጋሚ ተጨማሪ የበረሃ አንበጣ ወረራ መከሰቱን ተከትሎ በደቡብ ምሥራቅ የሚገኙ የኢትዮጵያ ከተሞች የበለጠ ተጋላጭ ሊሆኑ እንደሚችሉ ድርጀቱ ያስጠነቀቀ ሲሆን በቅርቡ 82 ሺሕ ሄክታር እርሻ ላይ በኦሮሚያ፣ በአማራ እና አፋር ክልሎች በተደረገ ዳሰሳ 32 ሺሕ ሄክታር የሚሆነው እንደተወረረ ተጠቁሟል።

የአንበጣ መንጋው 350 ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት ባለው ቦታ በቀን 1.8 ሚሊዮን ቶን እፅዋት የማውደም አቅም ያለው ሲሆን፣ አፋጣኝ እርምጃ ካልተወሰደ ቀላል የማይባል ጉዳት ሊያመጣ እንደሚችል ተገልጿል። እስከ አሁን በኢትዮጵያ የአንበጣ መንጋን ለመከላከል 2ሺሕ690 ሄክታር መሬት ላይ አንበጣውን ለማጥፋት የመድኀኒት ርጭት ተከናውኗል። ጉዳቱን ለመከላከል የተለያዩ እርምጃዎች እየተወሰዱ ቢሆንም እንደ ኦጋዴን ያሉ ቦታዎች ላይ አሁንም ወረራው እንደቀጠለ መረጃዎች ያሳያሉ።

ቅጽ 2 ቁጥር 54 ህዳር 6 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here