10ቱ በርካታ ቋንቋ የሚገኝባቸው አገራት

0
657

ቋንቋ የሰው ልጆች መግባቢያ ነው። በዓለማችንም ብዙ ቋንቋዎች ተፈጥረዋል። በተለያዩ አገራት ብቻ አይደለም፣ በአንድ አገር ውስጥም የተለያዩ ቋንቋዎች ይገኛሉ። ታድያ ይህ ሲሆን አገራት በማህበራዊ፣ ሳይንሳዊ ወይም ፖለቲካዊ ስምምነት ቋንቋ መርጠው ለጋራ መግባቢያነት የተወሰነውን ብቻ ይጠቀማሉ። የቋንቋቸውን ብዛትም ሐብት አድርገው ያቆዩታል።

በዚህ መሠረት ፓፕዋ ኒው ጊኒ በዓለማችን ብዙ ቋንቋ ካላቸው አገራት ተርታ ቀዳሚውን ይዛለች። በዓለም ካለው ቋንቋ 11.86 በመቶውም በዚህች አገር የሚገኝ ነው። የሚገርመው ደግሞ ከዚህ ሁሉ ቋንቋ ብሔራዊ ሆነው የሚያገለግሉት ሦስት ቋንቋዎች ብቻ ናቸው፤ እንግሊዘኛን ጨምሮ።

ኹለተኛዋ ደግሞ ኢንዶኔዥያ ናት፤ በኢንዶኔዥያ ያለው 742 ቋንቋ አገሪቱን በዓለማችን ካለው ቋንቋ 10.73 በመቶውን እንድትይዝ አስችሏታል። በአገሪቱ ብሔራዊ ሆኖ የሚያገለግለውም አንድ ቋንቋ ብቻ ነው። ናይጄሪያም ከአፍሪካ በቀዳሚነት በዓለም ደግሞ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ሆና በ516 ቋንቋ እና በዚህም ከዓለም 7.47 በሞውን በመያዝ ትገኛለች።

ይህ ዘገባ የሃያ አገራትን ዝርዝር ያስቀመጠ ነው። በዚህም ዝቅተኛው የቋንቋ ብዛት 115 ሲሆን ኢትዮጵያ በዚህ ዝርዝር አልተካተተችም። በአፍሪካ ግን ከናይጄሪያ ቀጥሎ ካሜሮን በዓለም 7ኛ በአፍሪካ ኹለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

ቪስታዋይድ የተሰኘው ድረ ገጽ በተለያዩ የዓለም አገራት የሚገኙ ቋንቋዎችን በተመለከተ በ2005 የተደረገን ጥናት መሠረት አድርጎ ነው መረጃውን ያወጣው። ቋንቋ በመወለድ፣ በማደግና በሞት ተፈጥሮ ስርዓት ውስጥ የሚያልፍ ቢሆንም ይህ የአሃዝ መረጃ አሁን ላይ ከፍተኛ የሚባል የቁጥር ልዩነት ይኖረዋል ተብሎ አይጠበቅም።

ቅጽ 2 ቁጥር 54 ህዳር 6 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here