የሩሲያ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ በነገው ዕለት ይጀመራል

0
1102

ለኹለተኛ ጊዜ የሚካሄደው የ”ሩሲያ-አፍሪካ” የመሪዎች ጉባኤ በነገው ዕለት በሴንት ፒተርስበርግ ከተማ ይጀመራል፡፡

ሩሲያ ከአፍሪካ አገራት ጋር ስላላት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የባህል እና መሰል ግንኙነቶች እና አሁናዊ ኹኔታ እና ወደፊት ሊደረጉ ስለሚገባቸው ጉዳዮች ላይ እንደሚመክቱ ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም ከጉባኤው በኋላ ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር አዳዲስ ስምምነቶች ታደርጋለች ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፤ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ግብይት ከዶላር ይልቅ ወደ ሌሎች ገንዘቦች እንደምታዞርም ይጠበቃል።

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭድሚር ፑቲን “በጣም አስፈላጊ ሲሉ” በገለጹት የሩሲያ አፍሪካ ጉባኤ ላይ፤ የአፍሪካ መሪዎች እንዲሳተፉ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡

በዚህ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ የኢትዮ-ሩሲያ በይነመንግሥታት የጋራ ኮሚሽን ጥምር ሰብሳቢ የሆኑት የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጅ ሚንስቴር ሚኒስትር በለጠ ሞላ፤ የኢትዮጵያ ልዑክ አባል ሆነው ወደ ሩሲያ ማቅናታቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

በጉባኤውም ከአፍሪካ ራሺያ ጉዳዮች ባሻገር የኢትዮ ራሺያን የተመለከቱ የጎንዮሽ ውይይቶች የሚደረጉና የጋራ ስምምነቶች በአገራቱ መካከል እንደሚፈረሙ ተነግሯል፡፡

በተጨማሪም የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በዚሁ የ”ሩሲያ-አፍሪካ” የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ፤ በዛሬው ዕለት ወደ ሩሲያ ማቅናታቸው ታውቋል።

በጉባኤው የአፍሪካ አገራት መሪዎች እንዲሁም አህጉራዊና አካባቢያዊ ድርጅቶች እና ማህበራት ይታደሙበታል ተብሎ ይጠበቃል።

በ2019 የመጀመሪያው የሩሲያ-አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ በሩሲያዋ ሶቺ ከተማ መካሄዱ የሚታወስ ሲሆን፤ ኹለተኛው የመሪዎቹ ጉባኤም ከነገ ጀምሮ ለሦስት ለተከታታይ ቀናት ፒተርስበርግ ከተማ ይካሄዳል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here