የቀድሞው የቤንሻንጉል ርዕሰ መስተዳደር ያረጋል አይሸሽም አረፉ

0
1116

የቀድሞው የቤንሻንጉል ክልል ርዕሰ መስተዳደርና የቤንሻንጉል ጉሙዝ  ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ቤጉዴፓ ሊቀ መንበር የነበሩት ያረጋል አይሸሽም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ያረጋል ቤንሻንጉል ክልልን ለረጅም ዓመታት በማስተዳደር ክልሉን የመሩ ሲሆን ከ1987 እስከ 2002 ድረስም አስተዳድረዋል ነበሩ።

ያረጋል ለ15 ዓመታት በርዕሰ መስተዳደርነት ካገለገሉ በኋላ ወደ ፌደራል ስልጣን በመምጣት የፌደራል ኅብረት ስራ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በመሆንም አገልግለዋል። ያረጋል ከዓመታት በፊት በተከሰሱበት የሙስና ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው በመገኘት ለሰባት ዓመታት በእስር መቆየታቸው የሚታወስ ነው።

ያረጋል ከአባታቸው አይሸሹም በርሃኔ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ሽታዩ ይማም ነበር በ1961 በድባጤ ከተማ የተወለዱት ። ከኮተቤ መምህራን ማሰልጠኛ ተቋም ከተመረቁ በኋላ በቀድሞው ባሌ ክፍለ ሀገር በመምህርነት አግለግለዋል። ያረጋል ትናነት ሰኞ ኅዳር 8/2012 ምሽት በገጠማቸው ድንገተኛ ሕመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።ያረጋል የአንድ ሴትና የሦስት ወንድ ልጆች አባት እንደነበሩ ኢዜአ ዘግቧል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here