“ጎጎት ለጉራጌ አንድነትና ፍትሕ ፓርቲ” የሕጋዊ አገር ዓቀፍ ፖለቲካ ፓርቲነት ማረጋገጫ ተሰጠው

0
374

ሰኞ ነሐሴ 8 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዐዋጁ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት “ለጎጎት ለጉራጌ አንድነትና ፍትሕ ፓርቲ” ሕጋዊ አገር ዓቀፍ ፖለቲካ ፓርቲነት ማረጋገጫ የምሥክር ወረቀት፤ ሐምሌ 18/2015 መስጠቱን አስታውቋል።

ጎጎት ፓርቲ ሕዳር 21/2015 ጊዜያዊ ፍቃድ አግኝቶ ለመስረታ የሚያስፈልጉ ቅድመ ኹኔታዎችን በማሟላት መጋቢት 3/2015 የመስራች ጉባኤውን ማካሄዱ ይታወሳል፡፡

ፓርቲው የመስራች ጉባኤውን አድርጎ ከተመሰረተ በኋላ በነበሩት ወራትም፤ በዋናነት የፓርቲው ተቋማዊ ቁመና በመቅረጽ እና ፓርቲው የሚመራባቸው ደንቦችና መመሪያዎችን ሲያዘጋጅ መቆየቱን ያስታወቀ ሲሆን፤ የፓርቲውን ዋና ጽ/ቤት አዲስ አበባ ላይ እንዲሁም የጉራጌ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን ወልቂጤ ከተማ ላይ መክፈቱን ገልጾም ነበር፡፡በዚህም መሰረት ፓርቲው በኢትዮጵያ የምርጫ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ሥነ‐ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 መሰረት ፓርቲ ለማቋቋም የተቀመጡ መስፈርቶች በማሟላቱ ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የአገር አቀፍ ፖለቲካ ፓርቲ የምዝገባ እና የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ ማግኘቱን ቦርዱ አስታውቋል፡፡

“ጎጎት ለጉራጌ አንድነትና ፍትሕ ፓርቲ” ጉራጌ ለአገር ከሚያበረክተው ዘርፈ-ብዙ አስተዋዕጾ አንጻር ተገቢውን ጥቅም እንዲያገኝና፤ ፓለቲካዊ ውክልናውም ከፍ እንዲል አበክሮ እንደሚሰራ በተለያዩ ጊዜያት በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫዎች ሲያስታውቅ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here