አርብ ነሐሴ 12 ቀን 2015 (አዲስ ማለዳ) 6 ዞኖችና 5 ልዩ ወረዳዎች በአንድ ክልል ለመደራጀት በተስማሙት መሠረት፤ አዲሱ የ “ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል” የምስረታ ጉባኤ በጋሞ ዞን አርባምንጭ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
ለኹለት ቀናት በሚካሔደው በዚህ ጉባኤም አዲሱ “የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል” በይፋ ተመስርቶ ሥራ ይጀምራል።
በዛሬው ዕለትም በሕገ-መንግሥት አጽዳቂ ኮሚሽን ጉባኤ ላይ በክልሉ ረቂቅ ሕገ-መንግስት ላይ ሰፊ ውይይት ተደርጎበት ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
በጉባኤው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አስፈፃሚ አካላት ስልጣንና ተግባር የሚደነግግ አዋጅ በማውጣት ክልሉን የሚመሩ አካላትን እንደሚሾምም ተመላክቷል።

በተጨማሪ የክልሉ ምክር ቤት ማቋቋሚያ አዋጅና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ማቋቋምን ጨምሮ ሌሎች አዋጆችን መርምሮ ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።



