በኦሮሚያ ክልል ምዕራብና ምስራቅ ሐረርጌ ዞኖች ግጭት የፈጠሩ ከ160 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

0
656

በወልድያ ዩኒቨርስቲ ተከስቶ የነበረውን ግጭት ሌላ መልክ እንዲኖረው እና ወደ ኦሮሚያ ክልል እንዲዛመት ሲያደርጉ የነበሩ 165 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን  የክልሉ የመንግስት ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ገልጿል። ተፈጥሮ ከነበረው ግጭት ጋር ተያይዞ በኦሮምያ ክልል በምስራቅ እና ምእራብ ሐረርጌ ኹለት ዞኖች ላይ ግጭት ለመቀስቀስ የሞከሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የክልሉ መንግሥት አስታውቋል።

ከግጭቱ ጋር በተያያዘ በምስራቅ ሐረርጌ 65 ሰዎች ሲያዙ በምእራብ ሐረርጌ ደግሞ 100 ተጠርጣሪዎች መያዛቸው ኢትዮ ኤፍ ኤም በዘገባው አስታውቋል።

በወልድያ ዩኒቨርስቲ ተከስቶ በነበረው ግጭት ምክንያትም የኹለት ሰዎች ሕይወት ያለፈ ሲሆን በንግድ እና በእምነት ተቋማት ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወሳል። በዚሁ ግጭት ተጎድቶ በሕክምና ሲረዳ የነበረ አንድ ተማሪ ከቀናት በኋላ ህይወቱ ማለፉን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁ የሚታወስ ነው።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here