በሕገ ወጥ መንገድ ጅማ ከተማ ሊራገፍ የነበረ ከ1 ሺሕ በላይ ባለ ሃያ ሊትር የምግብ ዘይት ተያዘ

0
787

በሕገ ወጥ መንገድ ተጭኖ ጅማ ከተማ የቡና መፈልፈያ መጋዝን ውስጥ ሊራገፍ የነበረ አንድ ሺህ 61 ባለ ሃያ ሊትር የምግብ ዘይት በቁጥጥር ስር ማዋሉን የጅማ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል። ኅብረተሰቡ ለፖሊስ በሰጠው ጥቆማ መሰረት ዘይቱን በቁጥጥር ስር ማዋል የተቻለ ሲሆን ፤ፖሊስ በቦታው ሲደርስም አሽከርካሪው የመኪናውን ግማሽ ጎታች ይዞ መሰወሩ አሰታውቋል።ፖሊስ አሽከርካሪውን ለመያዝ ጥረት እያደረገ መሆኑን የጅማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የኮሙዩኒኬሽን ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ገዛኸኝ አውግቸው ተናግረዋለ። በተያያዘ ዜና በተሳቢ የጭነት ተሽከርካሪ ባለ 20 ሊትር 250 ጀሪካን እና ባለ 5 ሊትር 150 ካርቶን የምግብ ዘይት ጭነዉ ከአዳማ ወረዳ ወደ አዋሽ በመጓዝ ላይ የነበሩ 3 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል። ተጠርጣሪዎቹ ለወረዳው ፖሊስ አዛዥ 100 ሺሕ ብር ጉቦ በመስጠት የተያዘውን ዘይት ለማስለቀቅ ቢሞክሩም የወረዳዉ ፖሊስ አባላት ግለሰቦቹን እና ገንዘቡን በመቀበል ለሕግ ማቅረባቸው ታውቋል ሲል ፋና ብሮድካስቲንግ ዘግቧል። ኅብረተሰቡ ሕገ ወጥ ድርጊቱን ተመልክቶ ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠቱ ምስጋና ያቀረቡት ኃላፊው ሕዝቡ መሰል ሕገ ወጥ ተግባራትን ሲመለከት ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት ወንጀልን በጋራ የመከላከል ድርጊቱ ቀጣይነት እንዲኖረው አሳስበዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here