ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 649 ነጥብ6 ሚሊዮን ብር አተረፈ

0
667

የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት በ2012 በጀት ዓመት  የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የዕቅዱን 108 በመቶ በማሳካት 649 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር አተረፈ። ድርጅቱ 598 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ለማትረፍ አቅዶ የነበረ ሲሆን  በጊዚያዊ ሂሳብ መረጃ መሠረት ከታክስ በፊት ብር 649.65 ሚሊዮን ብር ማትረፉን የመንግሥት  የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

ድርጅቱ ይህን ትርፍ ሊያገኝ የቻለው ገቢ ዕቃዎችን በባህር በማጓጓዝ፣በውጭ አገራት ወደቦች መካከል የጭነት አገልግሎት በመስጠት፣በመልቲ ሞዳል ወደ አገር ውስጥ ኮንቴይነርና ተሸከርካሪዎችን በመጓጓዝ፣በዩኒሞዳል ገቢ እና ወጪ ዕቃዎችን በማስተላለፍ፣በአገር ውስጥ ደረቅ ወደቦች ኮንቴይነርና ገቢ ተሸከርካሪዎችን በማስተናገድ እና ወጪ ጭነት በአገር ውስጥ በማሸግ ብር 6 ነጥብ67 ቢሊዮን ገቢ ለማግኘት አቅዶ ብር 5.82 ቢሊዮን ወይም የዕቅዱን 87 በመቶ በማግኘቱ እንደሆነ የሩብ ዓመቱ ዕቅድ አፈጻጸም በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ መሰብሰቢያ አዳራሽ ጥቅምት 27 ቀን 2012 ዓ.ም. በተገመገመበት ወቅት ተገልጿል፡፡

የዕቅድ አፈጻጸሙን ግምገማ የመሩት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ በየነ ገ/መስቀል ሲሆኑ፣የድርጅቱ ዋና ሥራአስፈጻሚ አቶ ሮባ መገርሳ ፣ ሌሎች የማኔጅመንት አባላትና የኤጀንሲው የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ዳይሬክተርና ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here