በአፋር ክልል የኮሌራ ስርጭት ጨምሯል ተባለ

0
792

በአፋር ክልል የኮሌራ በሽታ መከሰት ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ ከ 116 በላይ ሰዎች በበበሽታው መያዛቸው ተገልጿል፡፡አብዛኛዎቹ ታማሚዎችም በተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ በጉልበት ሠራተኛነት የተሰማሩ ሰዎች ናቸው ተብሏል፡፡

ለበሽታው መስፋፋት በአካባቢው በቂ የንፁህ ወሃ አቅርቦት አለመኖሩ እንዲሁም ውሃን ለማከም የሚረዱ ኬሚካሎች በስፋት አለመገኘታቸው በምክያትነት ተጠቅሷል፡፡

የክልሉ መንግሥትም የበሽታውን ስርጭት ለመቆጣጠር ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር በመተባበር ግብረ ኃይል አቋቁሞ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡
በዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት መረጃ መሰረት ኮሌራ፤ ቫይብሮ ኮሌራ በተባለ ተዋሲ አማካኝነት የሚመጣና አንጀትን የሚያጠቃ በሽታ ነዉ። በሽታዉ በዚህ ተዋሲ በተበከለ ምግብና ውኃ አማካኝነት የሚመጣ ሲሆን በድንገት የሚጀምሩ አጣዳፊ ተቅማጥ እና ተውከት ምልክቶቹ ናቸዉ።

የሰውነት ፈሳሽን በማሟጠጥና አቅም በማሳጣት ተገቢዉ ሕክምና ካልተደረገ በጥቂት ስዓታት ውስጥ ለሞት ሊዳርግ የሚችል በሽታም ነዉ ። በሽታዉ ተላላፊና በወረርሽኝ መልክ የሚከሰት ሲሆን የበሽታዉ ምልክት መታየት ከጀመረ ጀምሮ ባሉት አምስት ቀናት ውስጥ የመግደል ኃይሉ ከፍተኛ መሆኑን የዓለም አቀፉ የጤና ድርጅት መረጃ ያሳያል።

ይህ በሽታ ከወራት በፊት በኢትዮጵያ በአማራ፣ በትግራይ፤ በኦሮሚያ እና በሶማሌ ክልሎች እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ መከሰቱ ተገልፆ ነበር፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 55 ኅዳር 13 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here