10ቱ በአሜሪካ በብዛት የሚገኙ ብሔሮች

0
629

ወርልድ አትላስ የተባለው ድረ ገጽ በአሜሪካ በብዛት የሚገኙ ትውልዳቸው ወደ ኋላ ሲቆጠር ከተለያየ አገር የመጡ ወይም በአገሪቱ የተለያየ ብሔር (Ethnic Group) የሆኑትን በዝርዝርና በመቶኛ አስቀምጦ ነበር። እንደሚታወቀው አሜሪካ በብሔርም በዘርም የተለያዩና ብዝኀ ሕዝቦችን ይዛለች። ብሔር ሲባል መነሻቸው የተለያየ አገር የሆነ፣ ዘር ሲባል ደግሞ ጥቁርና ነጭ የሆኑ እንደሆነ ልብ ይሏል።

በዚህም መሠረት በአሜሪካ ከሚገኙ ሕዝቦች መካከል ከፍተኛውን ድርሻ የያዙት ጀርመናውያን እና አፍሪካ አሜሪካውያን (ጥቁር አሜሪካውያን) ናቸው። በቁጥሩ መሠረት አንድ መቶ ከሆኑ አሜሪካውያን መካከል ወደ 15 የሚጠጉት ጀርመናዊ መሠረት ያላቸው ሲሆኑ 12 የሚሆኑት ደግሞ የጥቁር ዘር ያላቸው ናቸው።
የሚገርመው አሜሪካውያን መሠረት አላቸው የሚባሉት ከእነዚህ ሁሉ ባነሰ ቁጥር የሚገኙ ናቸው። ወርልድ አትላስ እንደጠቆመው ከመቶ ሰዎች መካከል ሰባ ብቻ ከሌላ ብሔር/አገር ያልወጡ አሜሪካውያን ሆነው ይገኛሉ።

በዝርዝሩ ላይ ይህን የጠቀሰው ዘገባው፤ እንደውም ከደቡብ፣ ሰሜን እና ማዕከላዊ አሜሪካ እና አላስካ ነው ምንጫቸው የተባሉ ‹ንጹህ› አሜሪካውያን ከመቶ አሜሪካውያን በቁጥር ኹለት የሚጠጉ (1.6) ናቸው። እነዚህም በከፋ ድህነት ውስጥ የሚገኙ ናቸው ሲል መረጃው ያክላል። ይህም ነገር እውነትም አሜሪካን የብዝኀነት አገር ናት (multi-racial and multi-ethnic) እንድትባል አስችሏታል።

እነዚህ ብሔሮች በአሜሪካ ሊገኙ የቻሉት በተለያየ ምክንያት ሲሆን አፍሪካዊ ወይም ጥቁር አሜሪካውያን የሚባሉት በቀኝ ግዛት ዘመን በባርነት ተሸጠው የሔዱ፤ የተቀሩትና አብዛኞቹ ደግሞ የተለያየ መነሻ ባለው ስደት ወደ አሜሪካ የገቡ ናቸው።

ቅጽ 2 ቁጥር 55 ኅዳር 13 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here