ሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አቤቱታ አቀረበ

0
156

ሰኞ መስከረም 28 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ፤ “የክልሉ መንግሥት የፓርቲውን ሕጋዊ እንቅስቃሴ በሕገወጥ አካሄድ ለመግታት እየተደረገ ያለውን ድርጊት በአስቸኳይ እንዲቆም ይደረግልን” ሲል ለኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አቤቱታ አቅርቧል።

ፓርቲው ለምክር ቤቱ በጻፈው ደብዳቤ በአገሪቱ ሕግ መሠረት የተመሰረተና በሲዳማ ክልል የሚንቀሳቀስና የምክር ቤቱ አባል መሆኑን ጠቅሶ፤ ሲዳማ ክልላዊ መንግሥት በአገሪቱ ሕግ መሠረት የተቋቋመው ፓርቲ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ በአመራሩና በአባላቱ ላይ የተለያዩ ሕገወጥ ድርጊቶች፣ እስራት፣ ወከባና ስደት ሲያደርስ መቆየቱን ጠቁሟል።

አያይዞም “የክልሉ መንግሥት አሁንም በሕገወጥ መንገድ ምንም ወንጀል ባልሰሩት አባላትና አመራር እየዛተ፣ እያሰረና እያሳደደ ይገኛል።” ብሏል።

እስከ አሁን 20 አመራርና አባሎቻችን የታሰሩ መሆኑንና የፓርቲውን ሊቀመንበርን ጨምሮ ሌሎች 44 አመራርና አባላት ላይ በዘመቻ መልክ የወንጀል መጥሪያ አውጥቶ እያሳደደ እንደሚገኝም ፓርቲው በደብዳቤው ገልጿል።

በመሆኑም “ይህ በዘመቻና በሽብር መልክ የአገሪቱን ሕገ መንግሥታዊ መብት ተጠቅሞ የተደራጀው የፓርቲውን ሕጋዊ እንቅስቃሴ በሕገወጥ አካሄድ ለመግታት እየተደረገ ያለው የክልል መንግሥት ድርጊት በአስቸኳይ እንድዲቆም እንዲደረግልን።” ሲል ምክር ቤቱን ጠይቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here