ለሥራ ወደ ውጪ የሚጓዙ ዜጎችን በሕጋዊ መንገድ እንዲጓዙ የሚደግፍ የቴክኒክ ቡድን ተቋቋመ

0
214

ሰኞ መስከረም 28 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ለሥራ ወደ ውጪ የሚጓዙ ዜጎችን በሕጋዊ መንገድ እንዲጓዙና በመዳረሻ አገራት ችግር እንዳይገጥማቸው የሚያግዝ የቴክኒክ ቡድን ተቋቋመ።

ቡድኑ የተመሠረተው የሥራና ክኅሎት ሚኒስቴር ከዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር መሆኑ ተገልጿል።

የሥራና ክኅሎት ሚኒስቴር ከዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት በጋራ በሰጡት መግለጫ፤ ቴክኒካል ቡድኑ ዜጎች ለሥራ ከአገር ሲወጡ በሕጋዊ መንገድ እንዲወጡ የሚያስችል መሆኑን አመልክተዋል።

በተጨማሪም ለሥራ ወደ ውጪ የሚጓዙ ዜጎች አስፈላጊ ሥልጠናዎችን እንዲያገኙና ስለሚጓዙበት አገርም በቂ መረጃ ኖሯቸው የሚገባቸውን ክፍያ እንዲያገኙ የሚያስችል ነው መባሉን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

ቴክኒካል ቡድኑ ለሥራ ከአገር የሚወጡ ዜጎችን የሚገጥሟቸውን ችግሮች ይፈታል የሚል ተስፋም እንደተጣለበት ተመላክቷል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here