“የፈተና ውጤቱ ነገ ጠዋት 12 ሰዓት ላይ ይለቀቃል” ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ

ዘንድሮም የሬሜዲያል ፕሮግራም እንደሚኖር ተገልጿል

0
181

ሰኞ መስከረም 28 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የ2015 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ የመልቀቂያ ፈተና ውጤት ነገ ጠዋት 12 ሰዓት ላይ እንደሚለቀቅ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አስታውቀዋል፡፡

በዚህም መሰረት ተማሪዎች ነገ ጥዋት 12 ሰዓት ላይ በዌብሳይት እና በአጭር የጽሁፍ መልዕክት (SMS) ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል በዘንድሮ ዓመት በቀጥታ ያለፉ ተማሪዎች ቁጥር ውስን በመሆኑ፤ ዘንድሮም የሬሜዲያል ፕሮግራም እንደሚኖር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ አመላክተዋል፡፡

በዚህም መሰረት ፈተናውን ተፈትነው ማለፊያ ነጥብ (50 በመቶ) ሳያመጡ የቀሩ ተማሪዎች፤ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የማካካሻ ትምህርታቸውን ተከታትለው ፈተናውን በድጋሚ ይወስዳሉ ተብሏል፡፡

በ2014 የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ የመልቀቂያ ፈተና ከተፈተኑ ተማሪዎች መካከል የማለፊያ ውጤት ያመጡት 3 ነጥብ 3 በመቶ መሆናቸዉ የሚታወስ ነው፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here