አርብ ጥቅምት 2 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በዳውሮ ከተማ አጠቃላይ ሆስፒታል በተደረገ ቀዶ ሕክምና ከ65 ዓመት ወይዘሮ 11 ኪሎ የሚመዝን ዕጢ ማስወገድ መቻሉ ተገለጸ።
በሆስፒታሉ ለግለሰቧ የተደረገው ቀዶ ሕክምና ከ4 ሰዓታት በላይ መፍጀቱም ተነግሯል፡፡
በአሁኑ ሰዓት ታካሚዋ በሆስፒታሉ ውስጥ ሆና በጥሩ ጤንነት ላይ እንደምትገኝ ሆስፒታሉ መግለጹን የዳውሮ ኮሚንኬሽን ቢሮ አስታውቋል።



