ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሻገር የሞከሩ 13 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በኬንያ መያዛቸው ተገለጸ

0
182

ረቡዕ ጥቅምት 7 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በኹለት የተለያዩ ድንበሮች በታንዛኒያ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሻገር የሞከሩ 13 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የኬንያ ፖሊስ አስታውቋል።

7 ስደተኞች በማክታዉ ታይታ ታቬታ ወደ ታንዜንያ ለመሻገር የሚያግዛቸውን ሰው እየጠበቁ በነበሩበት ወቅት መያዛቸው የገለጸው የአገሪቷ ፖሊስ፤ ስደተኞቹ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመጓዝ አልመው ከአገራቸው መሰደዳቸውን ገልጿል።

በተጨማሪም ሌሎች 6 ስደተኞች ከሞያሌ ድንበር በመነሳት በኬንያ የተለያዩ ከተሞች አቋርጠው ወደ ታንዛኒያ ለመሻገር ሲሞክሩ በከሃንቻ ሚጎሪ መያዛቸውንም ተነግሯል፡፡

ስደተኞቹ እድሜያቸው ከ15 እስከ 25 እንደሆነ ፖሊስ የገለጸ ሲሆን፤ በኬንያ የመኖር ሕጋዊ ፍቃድ እንደሌላቸው በመረጋገጡ ወደ አገራቸው እንደሚመለሱ ፖሊስ ማስረዳቱን የአገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋሌ።

ባሳለፍነው ሳምንት 8 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በተመሳሳይ በኬንያ ቱርካና ስለመያዛቸው መዘገቡ ይታወሳል።

ከሞያሌ እስከ ናይሮቢ ድረስ ከ20 በላይ ኬላዎች ቢኖሩም፤ እነዚህን ኬላዎች በማለፍ በርካታ ስደተኞች ወደ ኬንያ መዲና እንደሚገቡ ይነገራል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here