ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ሰዎች ቁጥር ከ85 ሺሕ ማለፉ ተገለጸ

0
146

ሐሙስ ጥቅምት 8 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የሱዳን ጦርነት ከተቀሰቀሰ ግዜ ጀምሮ ወደ ኢትዮጵያ በመተማና ኩርሙክ ድንበሮች አቋርጠው የተለያዩ አካባቢዎች የገቡ ሰዎች ቁጥር ከ 85 ሺሕ 400 ማለፉን አለም ዓቀፍ የስደተኞች ድርጅት (IOM) ገልጿል።

እንደ አይ ኦ ኤም መረጃ እስከ እሁድ ጥቅምት 4/2016 ድረስ ድንበር አቋርጠው ከገቡት ስደተኞች ዉስጥ፤ 38 ሺሕ 560 የሚሆኑት ኢትዮጵያውያን፣ 31 ሺሕ 115 ያህሉ ሱዳናውያን እንዲሁም የተቀሩት 15 ሺሕ 821 የሚሆኑት የሦስተኛ አገር ዜጎች ሲሆኑ፤ በግጭቱ ሳቢያ ከሱዳን ተሰደው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ መሆናቸው ተጠቁሟል።

እንዱሁም ከእነዚህ ውስጥ 35 ሺሕ 440 ያህል ሴቶች ሲሆኑ፤ የተቀሩት 50 ሺሕ 056 ወንዶች መሆናቸውን መረጃው አመላክቷል።

በሱዳን ጦርነቱ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ 9 ሺሕ ሰዎች የሞቱ ሲሆን፤ 5 ነጥብ 6 ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ ከቤታቸው ንብረታቸው ተፈናቅለዋል፡፡ እንዲሁም በአጠቃላይ በአገሪቱ 25 ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎች የምግብ ድጋፍ እንደሚፈልጉ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል።

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ፤ በግጭቱ እየተሳተፉ ያሉ አካላት ሃላፊነታቸውን ተረድተው በአለም ዓቀፍ የሰብዓዊ ሕግ እንዲመሩ ሲል ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here