ማክሰኞ ጥቅምት 6 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ከጥቅምት 06/2015 ከለሊቱ 6:00 ሰዓት ጀምሮ በመስከረም ወር ሲሸጥ በነበረው እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።
በዚህም መሠረት በመስከረም ወር በነበረው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ማለትም፦
👉 ቤንዚን በሊትር 77 ብር ከ65 ሳንቲም
👉 ነጭ ናፍጣ በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም
👉 ኬሮሲን በሊትር 79 ብር ከ75 ሳንቲም
👉 ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 62 ብር ከ36 ሳንቲም
👉 ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 61 ብር ከ16 ሳንቲም ሆኖ እንደሚቀጥል ተገልጿል።



