አርብ ጥቅምት 9 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የመስከረም ወር አገር አቀፍ የዋጋ ግሽበት 28 ነጥብ 3 በመቶ ሆኖ መመዝገቡን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አስታወቀ፡፡
የተመዘገበው ግሸበት ካለፈዉ ተመሳሳይ ወራት ጋር ሲነፃፀር መጠነኛ ጭማሪ ማሳየቱ ተነግሯል።
በወሩ ውስጥ ከተመዘገበው የዋጋ ግሽበት ውስጥ ምግብ ነክ የሆኑት የዋጋ ግሽበት 27 ነጥብ 1 በመቶ ሲመዘገብ፤ 30 በመቶ ደግሞ ምግብ ነክ ያልሆኑ ድርሻዉን መያዛቸውም ተገልጿል።
በአጠቃላይ የዋጋ ግሽበቱ በነሐሴ ወር ከነበረት 28 ነጥብ 2 በመቶ ወደ 28 ነጥብ 3 በመቶ ጥማሪ ማሳየቱን ተቋሙ አስታውቋል፡፡



