በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን የሚንቀሳቀሱ ጸረ ሰላም ቡድኖች ላይ የማያዳግም እርምጃ እየተወሠደ መሆኑ ተገለጸ

0
178

ሰኞ ጥቅምት 12 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በሕገ ወጥ መንገድ በመደራጀት ሕዝብን ማጋጨትና ማፈናቀል ላይ አቅደው ሲሰሩ በነበሩ ፅንፈኛ ቡድኖች ላይ፤ የማያዳግም እርምጃ መወሰዱን የዕዙ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ሜጀር ጀኔራል ነገሪ ቶሊና ተናገሩ።

በዞኑ አቤ ደንጎራ ወረዳ “በሕገ ወጥ መንገድ ተደራጅተው ሰላማዊዉን ኅብረተሰብ ከቀዬው በማፈናቀልና በማሰደድ ይሰሩ በነበሩ የጸረ ሠላም ቡድኖች ላይ በተወሰደ ርምጃ ፅንፈኞችን መምታት” መቻሉን ነው የዕዙ ምክትል አዛዡ የገለጹት።

ዕዙ በተሰማራባቸው የግዳጅ ቀጠናዎች ሸኔ እና ፅንፈኛ ቡድኖች ላይ ርምጃ በመውሠድ ኅብረተሰቡን ወደ ሰላማዊ ኑሮው ለመመለስ በተሰራ ኦፕሬሽን፤ እነኝህ ቡድኖች የሕዝብ ስጋት ወደ ማይሆኑበት ደረጃ መድረሳቸውንም ገልጸዋል።“እነኝህ የጸረ ሠላም ቡድኖች በአካባቢው ኅብረተሰብ ላይ ያደረሱትን ውድመትና መፈናቀል ወደ ነበረበት ለመመለስ አመራሩ ኅብረተሰቡን በማወያየት በሁሉም የዕዙ ቀጠናዎች እየሰራ ይገኛል” ሲሉም መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።

ሜጀር ጀኔራል ነገሪ ቶሊና በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በአቤ ደንጎራ ወረዳ ተገኝተው የተፈናቀሉ ነዋሪዎችን መመልከታቸው የተገለጸ ሲሆን፤ በቀጠናው የሚገኘው ሠራዊት ግዳጅ አፈፃፀም ምን እንደሚመስል ከሠራዊቱ ጋር መወያየታቸውም ተነግሯል።

ግዳጅ እየፈጸመ የሚገኘውን የመከላከያ ሰራዊት የግዳጅ አፈፃፀም የማወያየትና የመገምገም ሥራ በመስራትም፤ የቀጣይ የሥራ አቅጣጫ ለሰራዊቱ መስጠታቸው ተገልጿል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here