”ወጣቶች ለአፍሪካ ሰላምና ደኅንነት” የተባለ የበጎ ፈቃድ እንቅስቃሴ በመጪው የካቲት በኢትዮጵያ በይፋ ይጀምራል

0
613

በአፍሪካ በበርካታ አገራት ላይ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው እና በርካታ አፍሪካዊያን ወጣቶችን በበጎ ፈቃደኝነት እያሳተፈ የሚገኘው Youth for Peace and Security Africa የተባለው በጎ ፈቃድ ተቋም በመጪው የካቲት 2012 በአዲስ አበባ በይፋ ስራ እንደሚጀምር የተቋሙ ዋና አስተባባሪ በኢትዮጵያ ሰማን አብዳለ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

እንደ ዋና አስተባባሪው ገለፃ በይፋ የሚጀምረው የወጣቶች በጎ ፈቃድ እንቅስቃሴ ከ1 ሽሕ በላይ በጎ ፈቃደኞችን ያቀፈ ሲሆን በተለያዩ የሙያ ዘርፍ የተሰማሩ ወጣቶችን ለኢትዮጵያ ብሎም ለአፍሪካ ሰላም ማሰለፍ እንደተቻለም አስታውቀዋል። ሰማን ጨምረው እንደገለፁት የበጎ ፈቃድ ኹነቱን በይፋ ለማስጀመር በሚደረገው መርሃ ግብር ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በወልቂጤ፣ ጂግጂጋ፣ ዲላ እና ሞያሌ ዝግጅቶች እንደሚደረጉም ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

ተቀማጭነቱን በምዕራብ አፍሪካዊቷ አገር ጋና ያደረገው ይኸው ድርጅት በተለያዩ አገራት ስለ አፍሪካ ሰላም የሚመክር እና በርካታ አፍሪካዊያን ወጣቶችን በማስተሳሰር ሰላምን ለማብሰር የሚሰራ ድርጅት እንደሆነ ሰማን ስለ በጎ ፈቃድ እንቅስቃሴው አስረድተዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here