ዳሰሳ ዘ ማለዳ ኅዳር 16/2012

0
560

1-የሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ሶዴፓ) ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የብልጽግና ፓርቲን ለመዋሃድ መወሰኑን አስታወቀ። የሶዴፓ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ዛሬ ኅዳር 16/2012 ጅግጅጋ ባካሄደው ስብሰባ ውሳኔ ማሳለፉን አስታውቋል።ሶዴፓ እንዳስታወቀው ብልፅግና ፓርቲ አደረጃጀትና የኢህአዴግ ውህደት ሶዴፓ የቆመለትን የአርብቶ አደር ማሕበረሰብ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም የሚያስጠብቅ እንዲሁም የሶማልኛ ቋንቋን የፓርቲው ብሄራዊ የስራ ቋንቋ የሚያደርግ መሆኑን አንስቷል። (ፋና ብሮድካስቲንግ)
……………………………………………………………………
2-በትግራይ ክልል የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭትን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ በመቀዛቀዙ ምክንያት በሽታው በወረርሽኝ ደረጃ ላይ እንሚገኝ የክልሉ ጤና ቢሮና አጋር ተቋማት አስታውቋል።በትግራይ ጤና ቢሮ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ የስራ ሂደት ባለቤት አስተባባሪ ፍስሃ ብርሃነ እንደገለጹት በሽታውን ለመከላከል በክልሉ ውስጥ ቀደም ሲል የነበሩ እንቅስቃሴዎች እየተቀዛቀዙ በመምጣቱ መሆኑን ገልጸዋል።የኢትዮጵያ ጤና ምርምር ኢንስቲትዩት ባለፈው ዓመት ባካሄደው ጥናት መሰረት በክልሉ የኤች አይ ቪ ኤድስ የስርጭት መጠን አንድ ነጥብ ሶስት በመቶ ያህል መድረሱን አስተባባሪው አመልክተዋል።(ኤዜአ)
……………………………………………………………………
3–የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ኅዳር 16/2012 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሄደ ሲሆን የጥላቻ ንግግርና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረበ ረቂቅ አዋጅን ለዝርዝር እይታ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መርቷል።በስብሰባው የፌዴራል የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት ረቂቅ አዋጅን እና የጥላቻ ንግግርና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የቀረቡ ረቂቅ አዋጅን የተመለከተ ሲሆን ፤ የፌዴራል የአስተዳደር ስነ-ስርዓትን ለመደንገግ በተዘጋጀ ረቂቅ አዋጅ ላይም መክሯል።(አዲስ ማለዳ)
……………………………………………………………………
4-ኢትዮጵያ እና ጃፓን ለመንገድ ግንባታ የሚውል የ89 ሚልዮን ዶላር ብድር ስምምነት ተፈራረሙ።ብድር የጅማ – ጭዳ – ሶዶ – ሳዉላ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታን ለማከናወን ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን የብድር ስምምነቱን በኢትዮጵያ የጃፓን አማባሳደር ማትሱንጋ ዳኡሲኬ እና የገንዘብ ሚንስትር ዴኤታው አድማሱ ነበበ ስምምነቱን ተፈራረመዋል።(አዲስ ማለዳ)
……………………………………………………………………
5-የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ አገልግሎት የሚሰጡ ሶስት ቅርጫፎችን ኅዳር 16/2012 በአዲስ አበባ ከተማ አስመርቋል።ባንኩ ሙሉ በሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት እንዲሰጡ የከፈታቸው አዳዲስ ቅርንጫፎችም አውቶብስ ተራ አካባቢ ፊት አውራሪ አመዴ ለማ ቅርንጫፍ፣ ቤተል አደባባይ ተቅዋ ቅርንጫፍ እና አለም ባንክ አደባባይ ሙስአብ ቅርንጫፍ መሆናቸውን አስታውቋል።(ፋና ብሮድካስቲግ)
……………………………………………………………………
6-የታዛኒያው ኤግዚም ባንክ በኢትዮጵያ ቅርጫፉን ሊከፍት መሆኑን አሰታወቀ።ኤግዚም ባንክ ቡድን በኢትዮጵያ ገበያ ውስጥ ሥራዎችን የጀመረ የመጀመሪያው የታንዛኒያ የገንዘብ ተቋም ሲሆን በአፍሪካ በሕዝብ ብዛት ኹለተኛ ደረጃ ባላት ኢትዮጵያ መዳርሻውን ሲከፍት አምስተኛው ቅርንጫፉን እንደሚሆን አስታውቋል።ባንኩ በዳሬሰላም ባወጣው መግለጫ በኢትዮጵያ እና በጅቡቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ለመክፈት ማቀዱን አስታውቋል።የባንኩ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሚስተር ጃፍሪ ማቱቱ እንዳሉት “የንግድ ሥራችን ተወካይ ጽህፈት ቤት በታህሳስ ወር 2019 ሙሉ በሙሉ ስራውን ይጀምራል ተብሎ ይጠበቃል” ብለዋል።(ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8)
……………………………………………………………………
7–በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሁከት ለመፍጠርና የመማር ማስተማሩን ሂደት ለማደናቀፍ ሲሞክሩ ተይዘው ከነበሩ 40 ተጠርጣሪዎች መካከል ሃያ አንዱ በምክርና በተግሳፅ ሲለቀቁ አስራ ዘጠኙ ተጨማሪ ምርመራ እየተካሄደባቸው መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አስታወቀ። የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አስራት አፀደወይን እንደተናገሩት፣ 38 ተማሪዎች፣ አንድ የዩኒቨርሲቲው ሰራተኛ እና አንድ ሌላ የግቢው ተማሪም ሰራተኛም ያልሆነ ግለሰብ በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ሕይወት ለማጥፋት፣ አካል ለማጉደል፣ ሽብር ለመፍጠርና የዩኒቨርሲቲውን ውስጣዊ ሰላም ለማናጋት ሲሞክሩ ተይዘው ጉዳያቸው በፖሊስ ሲታይ መቆየቱን ገልጸዋል።(ዶይቼ ቬለ)
……………………………………………………………………
8-በከተማ ልማት ዘርፍ የ10 ዓመታት ዕቅድ ላይ ያተኮረ ውይይት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።ውይይቱ በዋናነት በኢትዮጵያ የሚገኙ ከተሞችን በማሳደግ እና የስራ ዕድል ፈጠራ ላይ ያተኮረ ነው።በውይይቱ በከተማ ልማት ስራዎች ላይ የሚታዩ ችግሮችን በመቅረፍ በቀጣይ 10 ዓመታት ከተሞችን በተሻለ ሁኔታ ማልማት እንደሚቻል በመድረኩ ተነስቷል።(ዋልታ)
……………………………………………………………………
9-በኢፌዲሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ የሚመራ ከ50 በላይ አባላትን ያካተተ የፐብሊከ ዲፕሎማሲ ልዑክ ዛሬ ህዳር 16/2012 ወደ ኡጋንዳ ካምፓላ ይጓዛል።የፐብሊክ ዲፕሎማሲ የልኡካን ቡድኑ ከፓርላማ፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር፣ ከሃይማኖት ተቋማት፣ ከታወቂ ግልሰቦች፣ ከዩኒቨርሲቲ ምሁራን፣ ከኢትዮጵያ የንግድ ምክር ቤት፣ ከሴቶች የንግዱ ማህበረሰብ፣ ከስነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ከሚዲያ ተቋማት፣ ከኢትዮጵያ የባህል ቡድን የተወከሉ አባላትን ያካተተ መሆኑ ታውቋል።(የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here