የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚ ቡድን ጦር መሪ ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተገለፀ

0
460

የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚ ቡድን የጦር አበጋዝ ብርጋዴር ጀነራል ማሉላ ዶክ ባሳለፍነው ሳምንት ረቡዕ ባጋጠማቸው ቀላል ህመም ኢትዮጵያ ውስጥ በጋምቤላ ክልል ጋምቤላ ከተማ ህይወታቸው አልፏል። የሱዳኑ የዜና አውታር ኒያልማፔድ እንዳስታወቀው በጀነራሉ ህልፈት በርካቶች በተለይም ደግሞ የደቡብ ሱዳን ተቃዋሚ ቡድን አመራሮች ጥልቅ ሀዘን ውስጥ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።

ብርጋዴር ጀነራል ማሉላ ሞት የተሰማው ከጥቂት ቀናት አስቀድሞ በደቡብ ሱዳን የተቃዋሚ ቡድን የምዕራብ ኢኳቶሪያል ክንፍ አስተዳዳሪው ብርጋዴር አውጉስቲኖ ሞዲ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩ ሲሆን የአሁኑ ጀነራል ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ኹለተኛው ጀነራል መሆናቸው ነው።

ደቡብ ሱዳን ጆንግሌ ክፍለ ሀገር ቤህ ስቴት አስተዳዳሪ ጀነራል ሆት ዱዎል እንደገለፁት የጀነራ ሞት እጅግ አሳዛኝ እንደሆነና በተለይም ለወዳጅ ዘመድ እንዲሁም ለሉዎ እና ኑዌር ጎሣዎች መፅናናትን ተመኝተዋል። አያይዘውም ጀነራል ማሉላ ህይወታቸውን ለሕዝብ የሰጡ እና በቁርጠኝነት ሲታገሉ የኖሩ መሆናቸውን አውስተው፤ በቀጣይም የጀነራሉን ስራ በማስቀጠል ትግላቸውን ከዳር ለማድረስ እንደሚሰራም አሳስበዋል ሲል ኒያልማፔድ ዘግቧል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here