ዳሰሳ ዘ ማለዳ ኅዳር 19/2012

0
607

1-የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከፓርቲዎች ጋር ሲያካሂድ የነበረው ውይይት ባለመግባባት መበተኑ ታውቋል።የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በምርጫ ማስፈጸሚያ ሕጉ ዙሪያ ዛሬ ኅዳር 19/2012 ለማካሄድ ጀምሮት የነበረው ውይይት ባለመግባባት ተቋርጧል።ውይይቱ ሊቋረጥ የቻለው የፖለቲካ ፓርቲዎች ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ህግ አዋጅ ሆኖ ከመውጣቱ በፊት ረቂቁ ላይ የሰጡት አስተያየት ግብዓት ሆኖ አላገለገለም የሚል ሃሳብ ስላላቸው እንደሆነ ተገልጿል።(አዲስ ማለዳ)

……………………………………………………………..

2-ከአዲስ አበባ በሶስት አቅጣጫ ፈጣን መንገዶችን ሊገነባ መሆኑን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ።የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬከተር አቶ ሳምሶን ወንድሙ እንደገለጹት ከአዲስ አበባ ደብረ ብርሓን ፣ ከአዲስ አበባ ጎኃ ፅዮን፤ ከአዲስ አበባ ጅማ ፈጣን መንገድ የሚገነባባቸው መስመሮች ናቸው።ባለስልጣኑ እንዳስታወቀው ከአዲስ አበባ ሶስቱት መዉጫ እና መግቢያ በሮች ላይ የፈጣን መንገዶችን ለመገንባት ጥናት እየተካሄደ ሲሆን ጥናት ከተረጋገጠ በኋላም በቅድመ ተከተል ግንባታቸው እንደሚጀመርም ሳምሶን አስታዉቀዋል።(ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8)

……………………………………………………………..

3-የአዋሽ-ኮምቦልቻ የባቡር ፕሮጀክት የስራ አፈጻጸም ሁኔታን የትራንስፖርት ሚንስትሯ ዳግማዊት ሞገስ፣ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተመስገን ጥሩነህ እና የፌዴራል የሥራ ኃላፊዎች ጎብኝተዋል።ጉብኝቱ የፕሮጀክቱ የባቡር ሥራ በአብዛኛው ቢጠናቀቅም ለረጅም ጊዜ ጥያቄ ሆኖ የቆየው የኤሌክትሪክ አቅርቦት እጥረት የመፍትሔ አቅጣጫ ለማመልከት እንደሚረዳም ታምኗል።የሥራ ኃላፊዎቹ የባቡር መስመር ዝርጋታዎችን፣ የጥገና ማዕከል፣ የባቡር ጣብያውንና የኃይል ማከፋፈያ ማዕከላትን የሥራ አፈፃፀም ተመልክተዋል።(አብመድ)

……………………………………………………………..

4-በቅኝ ገዢዎች የተዘረፉ የአፍሪካ ቅርሶችን ለማስመለስ 15 ሚሊየን ዶላር መመደቡን ኦፕን ሶሳይቲ የተሰኘው ተቋም አስታወቀ።ድጋፋም አገራቱ ታሪካዊ እና ባህላዊ ቅርሶቻቸውን ለመመለስ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ለማገዝ የሚዉልመሆኑን አስታውቋል።አገራቱ በዋናነት በቀኝ ገዢዎቻቸው አማካኝነት ከተወሰዱባቸው ቅርሶች መካካል፣ በወርቅ እና በከበሩ እንቁዎች የተሰሩ ምስሎች የማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶች እና መዋእለ ዜናዎች ተጠቃሾች ናቸው።ከአፍሪካ አገራት መካከል ቅርሶቻቸው እንዲመለስላቸው ጥረት ካደረጉ እና እያደረጉ ከሚገኙ አገራት መካከልም ኢትዮጵያ ፣ናይጄርያ፣ ሴኔጋል እና ቤኒን እንደሚገኙበት ጠቅሷል።(ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8)

……………………………………………………………..

5-የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀመዉ ወጣት በ7ዓመት ከ5 ወራት ጽኑ እስራት በፅኑ እስራት ተቀጣ።ነሐሴ 4/2011 በግምት ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ሲሆን በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 013 ልዩ ቦታዉ መሪ ስኩል ኦፍ ቱሞሮ ትምህርት ቤት መግቢያ በር አቅራቢያ የግል ተበዳይዋ ከቤተ ክርስቲያን አምሽታ ስትመለስ አፍነዉ በመያዝና እንዳትጮህ በማስፈራራት ያልተያዘዉ ግብረ አበሩ እና ተከሳሹ ተፈራርቀዉ አስገድደዉ እያሰቃዩ መድፈራቸዉ በዐቃቤ ሕግ በማስረጃ በመረጋገጡ ተከሳሹ እጁን ለፖሊስ ከሰጠበት ጊዜ ጀምሮ እንዲታሰብለት በማሳሳብ በ7ዓመት ከ5 ወራት ጽኑ እስራት ይቀጣ ሲል ወስኖበታል።(አዲስ ማለዳ)

……………………………………………………………..

6- በተያዘው ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ብቻ በአዲስ አበባ ውስጥ 25 ሰዎች ለግንባታ እና ለቆሻሻ ማጠራቀሚያ ተብሎ በተቆፈረ ጉድጓድ ውስጥ ገብተው ህይወታቸው ሊያልፍ እንደቻለ ተገለፀ። በትናንትናው ዕለት ኅዳር 18/2012 በቦሌ ክፍለ ከተማ እና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ኹለት ሰዎች ውሃ ጉድጓድ ውስጥ ገብተው ሕይወታቸው ማለፉ ታውቋል። (አዲስ ማለዳ)

……………………………………………………………..

7-በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታዩትን ግጭቶች ሰግተው ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲዎች ያልገቡና ትምህርታቸው አቋርጠው ወደ ቅያቸው የተመለሱ የትግራይ ተማሪዎች መንግስት መፍትሔ ስላልሰጠን ከትምህርት ውጭ ሆነናል ሲሉ ቅሬታቸው ገለፁ፡፡ (ዶቼ ቬለ)

……………………………………………………………..

8- የምስራቅ አፍሪካ አገራት መንግሥታት በ13ኛው የኢጋድ የመሪዎች ላይ የቀይ ባህርን እና የኤደን ባህረለ ሰላጤን የሰላም ሁኔታ በተለመከተ ሰፊ ውይይት እያደረጉ እንደሚገኙ ታወቀ። (አዲስ ማለዳ)

………………………………………………………………

9- አዲሱ የሱዳን ፕሬዘዳንት አብደላ ሐምዶክ የኢጋድ የሊቀመንበርነትን ሥልጣን ከኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) በመቀበል የወቅቱ ኢጋድ ሊቀመንበር ሆነዋል።(አዲስ ማለዳ)

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here