ኢትዮጵያ እና ሳዑዲ አረቢያ በነዳጅና ኢነርጂ መስኮች በጋራ ለመስራት ተስማሙ

0
238

ሐሙስ ጥቅምት 29 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) ኢትዮጵያ እና ሳዑዲ አረቢያ በነዳጅና ኢነርጂ መስኮች በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል።

የትብብር ስምምነቱ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ እና በሳዑዲ አረቢያዉ የኢነርጂ ሚኒስትር ልዑል አብዱልአዚዝ ቢን ሰልማን አል ሳዑድ መካከል ነው የተፈረመው።

ስምምነቱ በሪያድ እየተካሄደ በሚገኘው የሳዑዲ አፍሪካ ኢኮኖሚ ኮንፍረንስ ላይ የተፈረመ ሲሆን፤ በዚህም ኹለቱ አገሮች በነዳጅ አቅርቦት፣ በኢነርጂ ቴክኖሎጂ ሽግግር እና በኢነርጂ ኢንቨስትመንት መስኮች በትብብር ለመስራት የሚያስችል መሆኑን በሪያድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

ይህም የኢትዮጵያን ነዳጅ አቅርቦት ከማረጋገጥ አና በኢነርጂዉ መስክ ለሚደረገው የልማት እንቅስቃሴ የበለጠ መነሳሳት እንደሚሆን ታምኖበታል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here