ረቡዕ ህዳር 26 ቀን 2016(አዲስ ማለዳ) ዳሸን ባንክ ባዘጋጀው ሁለተኛው ዙር የሥራ ፈጠራ ውድድር ላይ ተሳትፈው ላሸነፉ ተወዳዳሪዎች በዛሬው እለት በሸራተን አዲስ ሆቴል በተካሄደ ሥነ-ስርዓት ላይ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በሽልማት ሥነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አስፋው ዓለሙ ባንኩ ማሀበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት ከነደፋቸው ትልልቅ መርሃ ግብሮች አንዱ ይሀ የስራ ፈጠራ ውድድር መሆኑን ጠቁመው በመርሃ ግብሩ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ስድስት ሺህ ተወዳዳሪዎችን ማሳተፍና ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አመልክተዋል፡፡
ዳሽን ባንክ በድምሩ 2 ሚሊዮን 50 ሺህ ብር ለተወዳዳሪዎች ያበረከተ ሲሆን ፥ ከ6ሺ በላይ ተወዳዳሪዎች በባንኩ ቅርንጫፎችና ዋናው መስሪያ ቤት የውድድር ንድፈ ሃሳባቸውን በማቅረብ የተመዘገቡትን ከውድድሩ በፊት በአዲስ አበባ፣ አዳማ፣ ድሬዳዋ፣ ሃዋሳ፣ ባሀር ዳር እና ደሴ ከተሞች ስልጠና መሰጠቱ ተገልጿል።
ሶስተኛው ዙር የዳሸን ከፍታ ውድድር በቅርቡ እንደሚጁምርም በሽልማት ስነስርዓቱ ላይ ተነስቷል።


