10ቱ ቢዝነስ ለመጀመር ጥቂት ቀናት የሚወስድባቸው አገራት

0
1235

ምንጭ:ዓለም ባንክ (2017/18)

ሰዎች በግል ሥራ ለመሠማራት ሲጀምሩ የንግድ ፈቃድ ከማውጣትና የሥራ እቅዳቸውን ከማሳወቅ ጀምሮ የሚሔዱባቸው ሒደቶችና መንገዶች አሉ። የእነዚህ ሒደቶች አሰልቺነት አልያም ፈጣንና ቀልጣፋ መሆን ብዙዎች ወደ ንግድ ሥራ እንዳይሠማሩ የሚያሸሽ አልያም የሚያበረታታ ሲሆን ያታያል።

ታድያ ሊጠናቀቅ ቀናት ከቀሩት የአውሮፓውያኑ 2019 ዓመት ቀደም ብሎ የዓለም ባንክ ባወጣው ዘገባ፤ የንግድ ሥራን ለመጀመር ጥቂት ቀናት ብቻ የሚወስድባቸውን አገራት በዝርዝር አስቀምጧል። በዚህም መሠረት ኒውዚላንድ ከአንድ ቀንም ያነሰ በሰዓታት በሚቆጠር ጊዜ ውስጥ የንግድ ሥራ የሚጀመርባት አገር በመሆን ተመዝግባለች። ካናዳ አንድ ቀን ተኩል ሲወስድ ፈረንሳይ ውስጥ የንግድ ሥራ ለመጀመር ሦስት እና ተኩል ቀን ይወስዳል።

የ18 አገራት ዝርዝር በተቀመጠበት በዚህ የዓለም ባንክ ዘገባ ላይ፤ ከአፍሪካ አገራት መካከል የንግድ ሥራ ለመጀመር ጥቂት ቀናት የሚወስደው በናይጄሪያ ሲሆን ይህም ወደ 19 ቀን የሚጠጋ (18.9) ነው። ከናይጄሪያ ቀጥሎ ደቡብ አፍሪካ ንግድ ሥራ ለመጀመር 45 ቀናትን ይወስዳል።

ቅጽ 2 ቁጥር 56 ኅዳር 20 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here