ለማ መገርሳ የኢሕአዴግን ውሕደት ተቃወሙ

0
251

የመከላከያ ሚኒስትር፣ የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀ መንበር እንዲሁም የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ለማ መገርሳ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የሚቀነቀነውን የመደመር ፍልስፍና እንደዚሁም የብልፅግና ፓርቲ አስፈላጊነትና ወቅታዊነት ላይ እንደማይስማሙ ገለጹ።

ለማ ከአሜሪካ ድምፅ ራዲዮ የኦሮምኛ ፕሮግራም ጋር ባካሔዱት ቃለ ምልልስ እንደገለፁት፣ በግላቸው ከመጀመሪያ ጀምሮ የፓርቲውን ውህደት ሲቃወሙ የቆዩ መሆኑን ያስረዱ ሲሆን፤ ይህንንም ከመጀመሪያው ጀምሮ ለኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና በፓርቲው ውስጥ ለሚመለከታቸው ሁሉ መግለፃቸውን አስረድተዋል።

‹‹መዋሃዱ ትክክል አይደለም፤ ከሆነም በችኮላ መሆን የለበትም›› ሲሉ ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ገልፀዋል።
የኢሕአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባካሔደውና የብልጽግና ፓርቲ መተዳደሪያ ደንብ እና ፕሮራግም ላይ ተወያይቶ ይለፍ ብሎ ባፀደቀበት ጉባኤ ላይ ተገኝተው የነበሩት ለማ፣ በወቅቱ ስለነበረው የድምጽ አሰጣጥ ሒደቱ ለማብራራት ጊዜው አሁን አይደለም ሲሉም ገልጸዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ከሕውሓት ውጪ ያሉ የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶችና አምስት አጋር ፓርቲዎች እየመሰረቱት ያለ አገር አቀፍ ፓርቲ ነው።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here