ኢትዮጵያ በጅቡቲ የባህር ኃይል ልታሰፍር መሆኑ ተገለፀ

0
759

ኢትዮጰያ አዲስ የምታደራጀውን የባህር ኃይል በጅቡቲ ልታሰፍር እንደሆነ ካፒታል ጋዜጣ ዘግቧል። በጅቡቲ የሚሰፍረው አዲሱ የባህር ኃይል የዋና ዕዝ ጣቢያው በባህር ዳር እንደሚሆንም ለማወቅ ተችሏል። የኢህአዴግ ስልጣን ዘመን እስከ ጀመረበት 1983 ድረስ የነበረውን የኢትዮጵያ ባህር ኃይልን ትንሳኤ ለማብሰር እየተሰራ እንደሆነ ዘገባው አመላክቷል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የባህር ኃይሉ ካምፕ የትሊሆን እንደሚችል የተለያዩ መላ ምቶች ሲሰነዘሩ ቆይተዋል። ከመላምቶች ውስጥም ኤርትራ፣ ጅቡቲ እና ሱዳን በዋናነት የተጠቀሱ ሲሆን ምንጮች ለካፒታል ጋዜጣ እንደተናገሩት የባህር ኃይሉን በጅቡቲ ለማስፈር  የኢትዮጵያ መንግስት መወሰኑን ለማወቅ ተችሏል። አዲሱ በመቋቋም ላይ የሚገኘው የባህር በብረታብረት እና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ጊዜያዊ ቢሮ ያለው ሲሆን በአማራ ክልል ርዕሰ መዲና ባህር ዳር ለሚገነባው የዋና ማዘዣ ጣቢያ ባህር ኃይሉን በማቋቋም እና በመምራት ረገድ ብርጋዴር ጀነራል ክንዱ ገዙ በዋናነት እየመሩት እንደሚገኙ ታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here