10ቱ የንግድ ሥራ ለመሥራት የሚቀልባቸው የአፍሪካ አገራት

0
356

ምንጭ:ዓለም ባንክ (2017/18)

ቅኝ ግዛት ሲደቁሳት፣ የእርስ በእርስ ጦርነት ሲያምሳት የኖረችው አፍሪካ ከአኅጉራት በድህነት ደረጃ ከሚቀድሙት መካከል ሆና ዘመናት ተቆጥረዋል። ይሁንና አሁን አሁን በተለይም በኢኮኖሚው የተለያዩ ለውጦችና መሻሻሎች እየታዩ ስለመሆናቸው ዓለም ባንክ ጥናትን መሠረት አድርጎ አስቀድሞ በሠራውና ከወር በፊት ይፋ ባደረገው ዘገባ ላይ አቅርቧል።

በአውሮፓውያን አቆጣጠር ልንቀበለው በደረስንበት 2020፣ ንግድ ሥራ ውስጥ ለመግባት ኢኮኖሚያቸው አያስቸግርም ተብለው ከተቀመጡ አገራ መካከል ሞሪሺስ ቀዳሚውን ደረጃ ይዛለች። ምንም እንኳን ናይጄሪያ እና ቶጎ ኢኮኖሚያቸው የተሻሻለ አፍሪካዊ አገራት ሆነው በዓለም ባንክ የተዘመገቡ ቢሆንም፤ እነዚህ አገራት በቀላሉ ንግድ ሥራ የሚጀመርባቸው አይደሉም። በአንጻሩ ሞሪሺየስ ቀዳሚ ስትሆን ሩዋንዳ አና ሞሮኮ ኬንያን አስከትለው በዝርዝሩ በተርታ ተቀምጠዋል።

190 አገራት በተካተቱበት በዓለም ዝርዝር ላይ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት አፍሪካዊ አገራት ደቡብ ሱዳን 185ኛ፣ ኤርትራ 189ኛ እና ሶማሊያ 190ኛ ናቸው። ኢትዮጵያ በዚህ ዝርዝር ውስጥ 159ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠች ሲሆን፣ ጎረቤት አገር ኬንያ ከኢትጵያ በርቀት 56ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች። ዩጋንዳ 116ኛ እንዲሁም ታንዛንያ 141ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ። ሁሉም ታድያ ከቀደመው ዓመት ደረጃቸው ጋር ሲነጻጸር ቢያንስ ሦስት እና አራት ደረጃን ከፍ እንዳሉ የዓለም ባንክ ዘገባ ጨምሮ አካትቷል።

ቅጽ 2 ቁጥር 57 ኅዳር 27 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here