14ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው

0
864

14ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት አዘጋጅነት በአዲስ አበባ ከተማ እየተከበ ይገኛል። “ህገ-መንግስታዊ ቃልኪዳናችን ለዘላቂ ሰላም”! በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ እየተከበረ የሚገኘው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን ኹሉም የኢትዮጵያ ሕዝቦች በአንድነት የሚገናኙበት ቦታ እንደሆነም በበዓሉ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተናግረዋል።

የዘንድሮውን የብሔር ብሔረሰቦች በዓል ልዩ የሚያደርገው የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች የጋራ ቃል ኪዳን የሆነው የኢፌዲሪ ሕገ መንግስት 25ኛ ዓመት የልደት በዓል በሚከበርበት መሆኑን የኢፌዲሪ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ኬሪያ ኢብራሒም አስታውቀዋል። ኬሪያ አያይዘውም ሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነቱ በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልና ብዝኃነት በዲሞክራሲያዊ መንገድ ከተያዘ ጥንካሬ እና ውበት እንደሚሆንም ጨምረው ገልጸዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here