በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ አጣሪ የጥላቻ ንግግር እና ሐሰተኛ መረጃን በተመለከተ ተቃውሞ እንዳላቸው ገለፁ

0
445

በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የነፃ ሐሳብና በነፃነት ሀሳብን መግለጽ ጥበቃና አበረታች ልዩ መርማሪ ዴቪድ ካየ በቅርቡ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ለውይይት ቀረበውን የጥላቻ ንግግርና የሐሰት መረጃን በተመለከተ ተቃውሞ እንዳላቸው አስታወቁ። ዛሬ ኅዳር 29/2012 በአዲስ አበባ በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን አዳራሽ  መግለጫ የሰጡት ልዩ አጣሪው ረቂቁ ወደ ሕዝብ ተወካዮች የቀረበበት መንገድ ሕጋዊ አካሔዱን ባልተከተለና የሚመለከታቸውን አካላት ባላሳተፈ መልኩ በጥድፊያ የተደረገ ነው ሲሉ ምክንያታቸውን አስታውቀዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ረቂቁ በግልጽ ያላስቀመጣቸው እና ብዥታን የሚፈጥሩ በርካታ ጉዳዮች መኖራቸው እና ይህም በክልል እና በፌደራል ላይ ለሚገኙ የስራ ኃላፊዎች ያልተገደበ ሥልጣን እንዲኖራቸው እንደሚያደርግ አስታውቀዋል። ሐሳብን በነፃነት የመግለጽ መብት በኢትዮጵያ በተመለከተ ጥናት ያካሔዱት ዴቪድ የመጨረሻ የጥናታቸውን ውጤት ይፋ ባደረጉበት መግለጫ በጥላቻ ንግግር እና በሐሰተኛ መረጃን ማሰራጨት በተመለከተ በርካታ ግለሰቦችን ማናገራቸውን ተናግረዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here