ኢትዮጵያ ውስጥ መፈንቅለ መንግስት እንዳይሳካ ተደርጎ ነው ተቋማት የተገነቡት- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ 

0
194

ሐሙስ ሰኔ 27 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) እየተካሄደ በሚገኘው 36ኛ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያ ውስጥ መፈንቅለ መንግስት አይሳካም አሉ።

“የሆኑ አባቶቻችን” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጠሯቸው አካላት በቅርቡ ኢትዮጵያ ውስጥ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ሲመካከሩ ነበር ብለው ኢትዮጵያ ውስጥ መፈንቅለ መንግስት አይታሰብም በማለት ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ “እኛ ወታደሮች ነን፤ መፈንቅለ መንግስት እንዳይካሄድ አድርገን ነው ተቋማትን የገነባነው” በማለት “አትድከሙ” በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።

“የማይሳካው ነገር ተሳካ ብለን” መፈንቅለ መንግስት ቢደረግ ኢትዮጵያን ሌላ ሱዳን ነው እንጂ የምትሆነው “ሀገር ሆነን፤ እኛም መንግስት ሆነን” አንቀጥልም ሲሉም ዐቢይ አህመድ ለምክር ቤት አባላቱ ተናግረዋል።

በአማራ ክልል እየተካሄደ ስላለው ጦርነት ደግሞ “ከገባህ መግጠም ነው፤ አለመግባት ነው እንጂ” በማለት የተናገሩት ዐቢይ አህመድ መንግስታቸው ምንጊዜም ለሰላም ዝግጁ እንደሆነ ገልጸዋል።

ህዝቡ በመንግስት ላይ እምነት ጎድሎታል ለተባለው ሃሳብ “ህዝቡን ከእናንተ በላይ እናውቀዋለን” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ህዝቡ እንዴት ነው መንግስት የሰራለትን ትቶ መንገድ የዘጋበትን፣ ትምህርት ቤት የሰራለትን ትቶ ትምህርት እንዳይማር ያደረገውን የሚያምነው? በማለት ለጥያቄው ጥያቄ አቅርበዋል።

በተጨማሪም እስረኛ በመፍታት፣ አብረን እንስራ በማለት፣ ለድርድር ክፍት እንሁን በማለት አንታማም ሲሉ የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግስት ደካማ አይደለም፤ መንግስት ደካማ መሆን ቢፈልግ እንኳን ህዝቡ እንዳይፈቅድለት በማለትም አሳስበዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here