የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሺያው ከመደረጉ በፊት የሠነድ ምዝገባቸው የተከናወኑ እና ተቀባይነት ያገኙ ሠነዶች በበፊቱ የምንዛሪ ተመን እንደሚቀጥሉ ተገለጸ

0
345

ዓርብ ነሀሴ 10 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ አዲሱን መመሪያ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመረበት ሐምሌ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በፊት የሠነድ ምዝገባቸው የተከናወኑ እና ተቀባይነት ያገኙ ሠነዶች በበፊቱ የምንዛሪ ተመን እንደሚቀጥሉ የጉምሩክ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ከውጭ ምንዛሬው በፊት በፊት የሠነድ ምዝገባቸው የተከናወኑ እና ተቀባይነት ያገኙ ሠነዶች በበፊቱ የምንዛሪ ተመን ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡

ኮሚሽኑ ባለው የአሠራር መመሪያ መሠረት የገቢ ዕቃዎችን ሠነድ በመፈተሽ ወደ ሀገር እንዲገቡ እያደረገ እንደሆነ አስረድተዋል።
በምንዛሪ ግብይቱ ላይ ባለው ለውጥ ምክንያት የተለያዩ ጥያቄዎች አሉ ያሉት ኮሚሽነር ደበሌ ” ከሕግና መመሪያ ውጭ የተሠራም ሆነ የሚሠራ ሥራ የለም ሲሉ ገልጸዋል።

እኛ የሥራ_መመሪያዎችን ለደንበኞቻችን ሁሉ የማሣወቅ ሥራ እየሠራን ነው ፤ በአሠራር ሂደት ላይ ያሉ ጉዳዮችን ጠንቅቆ ማወቅ ያስፈልጋል ሲሉ ነው ኮሚሽነር ደበሌ ያስታወቁት፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here