ዓርብ ነሀሴ 10 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በኢትዮጵያ የሚካሄደውን አለም አቀፍ የቦክስ ውድድር አስመልክቶ ተወዳዳሪዎች ከተጋጣሚዎቻቸው ጋር ፊት ለፊት የመገናኘት የክብደት መለካት እና የሚዲያ ትውውቅ ፕሮግራም በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም አካሂደዋል::
በአጠቃላይ 7 ውድድሮች የሚከናወኑ ሲሆን 12 የውጭ ሀገር እና ሁለት ኢትዮጵያውያን ይሳተፉሉ::
ሞዛምቢክ ጋና ሞሮኮ ታንዛኒያ ካዛኪስታን ኡዝቤኪስታን ሩሲያ ናይጄሪያ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊከ ኦፍ ኮንጎ እና ዛምቢያ በውድድሩ ተወክለዋል::
በውድድሩ ኢትዮጵያ በሁለት ቦክሰኞች ትወከላለች:: የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮንስታብል አቡበከር ሰፉን በ60 ኪሎ የጋና አቻውን ይገጥማል:: በ75 ኪሎ የአዲስ አበባ ፖሊሱ ም/ሳጅን ተመስገን ምትኩ ከሞሮኮ አቻው ጋር እንደሚፋለም ታውቋል::
የአፍሪካ ቦክሲንግ ኮንፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢያሱ ወሰን ለዋናው የ58 ኪሎ ግራም ውድድር ቀበቶውን ይዘው ቀርበዋል::
የአፍሪካ ቦክስ ኮንፌዴሬሽን ዋና ቢሮ አዲስ አበባ መከፈቱን ተከትሎም የምርቃት ፕሮግራም በነገው ዕለት በዩኒቲ ፓርክ እንደሚከናወን ተገልፆል::



