10ቱ የገና ዛፍ በብዛት ያስገቡ አገራት

0
600

የገና በዓልና የፈረንጆች አዲስ ዓመት ሲከበር ለበዓሉ ድምቀት ከሚሰጡት መካከል የገና ዛፍ አንደኛው ነው። አልፎም በቁመት፣ በስፋትና በዛፉ ላይ በሚሰቀሉ አምፑሎች ብዛት አገራት የገና ዛፎችን ሲያወዳድሩና ሲያነጻጽ ማየት የተለመደ ነው። ይህም የገና በዓልና የፈረንጆች አዲስ ዓመት መግቢያ ትዕይንት ነው።

ታድያ እነዚህን የገና ዛፎች ሁሉም አገራት በየአገራቸው በገፍ አያመርቱም። ይልቁንም አውሮፓዊቷ አገር ዴንማርክ በብዛት የገና ዛፍን ለውጪ ገበያ በማቅረብ ትታወቃለች። በዐስርቱ ዝርዝርም አገራቱ ከዴንማርክ በሚያስገቡት የገና ዛፍ መጠን ድረሻ ተቀምጠዋል።

በዚህ መሠረት ታድያ በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2018 የገና ዛፍን ከዴንማርክ ገዝታ ወደ አገሯ በማስገባት ጀርመን ቀዳሚ ስፍራ ይዛለች። በአሃዝ ሲሰላ፤ ዴማርክ ለውጪ ገበያ ከምታቀርበው የገና ዛፍ ውስጥ 43 በመቶውን ጀርመን ገዝታለች ማለት ነው። ፈረንሳይ ደግሞ በ11 በመቶ በብዙ ልዩነት ትከተላለች። በመቀጠል ያሉት አገራት ተቀራራቢ መጠን ያለው የገና ዛፍን ከዴንማርክ ገዝተው ወደ አገራቸው ያስገባሉ። በዝርዝሩ አይስፈር እንጂ ሮማንያም 4 በመቶ በማስገባት ከነ ፖላንድ መካከል ትገኛለች።

‹ስታቲስታ› የተሰኘው ገጽ ባነበበው መረጃ መሠረት፤ ከእነዚህ አገራት ውጪ የሚገኙ ቀሪ የዓለም አገርት፣ ዴንማርክ ለውጪ ገበያ ከምታቀርበው የገና ዛፍ ውስጥ 6 በመቶውን የሚቀራመቱ ናቸው።

ቅጽ 2 ቁጥር 61 ታኅሣሥ 25 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here