አቶ ጌታቸው ያደረጉትን ሹም ሽር እንደማይቀበለው በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት አስታወቀ

0
499

እሁድ ነሐሴ 19 ቀን 2016 ( አዲስ ማለዳ)   በጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ የተደረገውን ሹም ሽር እንደማይቀበለው በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት አስታውቋል።

በእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ” በማንኛው የሃላፊነት እርከን በራስ ፍላጎት የሚደረግ የስራ ምደባና ሹምሽር ተቀባይነት የለውም ” ብሏል።

የእነ ደብረፅዮን (ዶ/ር) ህወሓት ለሁሉም የዞንና የወረዳ የድርጅቱ ፅህፈት ቤትን ጠቅሶ ባሰራጨው ደብዳቤ ፥ ” ከሰርዓታዊና ተቋማዊ አሰራር ውጪ የሚካሄዱ የስራ ምደባዎች ህገወጥ ብቻ ሳይሆኑ ተጠያቂነትን ያስከትላሉ ” ሲል አሳስቧል።

የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ነሃሴ 17/2016 ዓ.ም በህወሓት የፓሊት ቢሮ አባልዋ ወ/ሮ ሊያ ካሳ ምትክ ፀጋይ ገብረተኽለ ገ/ክርስቶስ የደቡባዊ ምስራቅ ዞን አስተዳዳሪ አድርገው ስለመሾማቸው አዲስ ማለዳ መዘገቧ ይታወሳል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here