ዕረቡ ነሐሴ 29 ቀን 2016 (አዲስ ማለዳ) በኤሌክትሪክ አገልግሎት ታሪፍ ላይ የተደረገው ማስተካከያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ሰኔ 13ቀን2016 ዓ.ም ማጽደቁ ይታወሳል።
ይህ ተከትሎ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የታሪፍ ማሻሻያው ከመስከረም 1ቀን2017 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል።
የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ሽፈራው ተሊላ የታሪፍ ጭማሪው የደንበኞችን የኃይል የአጠቃቀም መሰረት ያደረገ መሆኑን አንስተዋል።
በመሆኑም የቤት ደንበኞች፤ የንግድ ተቋማት፤ ዝቅተኛ ኢንዱስትሪ፤ ከፍተኛ ኢንዱስትሪ እንዲሁም የመንገድ መብራት ተጠቃሚዎች በሚል መከፋፈሉን አስታውቀዋል።
የቤት መብራት ተጠቃሚዎችን በተመለከተ ” እንደ አጠቃቀማቸው አሁን ከሚከፍሉት እና ጭማሪ ከተደረገበት መካከል ያለውን ልዩነት ሲከፍሉ እንደ አጠቃቀማቸው ድጎማ ተደርጓል ብለዋል።
ድጎማውም 50KW በታች ለሚጠቀሙ ደንበኞች ያለውን ልዩነት 75 በመቶ የሚሆነውን፣ ከ50KW እስከ 100KW ለሚጠቀሙ ደንበኞች ያለውን ልዩነት 40 በመቶ በተመሳሳይ መልኩ እንደየ አጠቃቀም እና ፍጆታ እና ከ500KW በላይ የሚሆነውን ደግሞ ሌላውን ተጠቃሚ የሚደግፉበት የጎንዮሽ ድጎማ ሥርዓት ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል፡፡
የአከፋፈሉ ሁኔታም እንደ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገለጻ የተደረገው የታሪፍ ማሻሻያው (የተጨመረው 6 ብር) የሚከፈለው በአንድ ጊዜ ሳይሆን በ16 ዙር በሚደረግ የሂሳብ ማስተካከያ ከመስከረም 1 /2017 ጀምሮ በአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሆነ አስታውቀዋል።
አክለውም 50KW/hr የሚጠቀሙ ደንበኞች አሁን የሚከፍሉት 27 ሳንቲም እንደሆነ እና ከመስከረም ጀምሮ የሚከፍሉት 35 ሳንቲም እንደሚሆን ገልጸዋል።



