10ቱ በጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት የሥራ ዕድል የተፈጠረባቸው ክልሎች

0
479

ምንጭ:የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ (2018/19)

ምንጭ፡ – የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው የ2018/19 ዓመታዊ ዘገባ ላይ፣ በበጀት ዓመቱ 110 ሺሕ 253 አዳዲስ ጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት መፈጠራቸውን ይገልጻል። በዚህ መሠረት ከዚህ አሃዝ ውስጥ 30 በመቶ የሚጠጋው ወይም በቁጥር 33 ሺሕ 047 የሚሆኑት ተቋማት በኦሮሚያ ክልል የተመሠረቱ መሆናቸውን ዓመታዊ ዘገባው አካትቷል።

ታድያ እነዚህን ጨምሮ በዘጠኙ ክልሎችና በኹለቱ ከተማ መስተዳድሮች የሚገኙት ጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት በድምሩ 882 ሺሕ 098 የሥራ እድሎች መፍጠር ችለዋል። በዚህም መሠረት ተቋማቱ በብዛት የሚገኙበት የኦሮሚያ ክልል በሥራ እድል ፈጠራም ከአስርቱ ቀዳሚውን ደረጃ የያዘ ሆኗል። በመቀጠል አማራ ክልል እና አዲስ አበባ ከተማ ኹለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

በዝርዝሩ የመጨረሻ ደረጃ ላይ የተቀመጠው የአፋር ክልል ነው። በብሔራዊ ባንክ ዓመታዊ ዘገባ መሠረት፣ በአፋር ክልል ምንም ዓይነት አነስተኛና ጥቃቅን ተቋም አልተመዘገበም። ያም ሆኖ የብድር አገልግሎት እየተሰጠ ለ2 ሺሕ 315 ዜጎች የሥራ እድል ሊፈጠር የቻለበት ክልል ነው። በአንጻሩ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአስራ አንደኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ክልል ሲሆን፣ ምንም እንኳን በድምሩ ካሉት ጥቃቅን እና አነስተኛ ተቋማት ውስጥ ከአፋር በተሻለ 0.7 በመቶ የሚሆኑት በዚህ ክልል የሚገኙ ቢሆንም፤ ሊፈጠር የቻለው የሥራ እድል ግን 2 ሺሕ 197 ብቻ ነው።

ቅጽ 2 ቁጥር 62 ጥር 2 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here