ኹለት የትግራይ ቴሌቪዥን የአማረኛ ክፍል ባልደረቦች በአሶሳ መታሰራቸውን ትግራይ ቴሌቪዥን አስታወቀ

0
643

አዲስ አበባ የሚገኘው የትግራይ ቴሌቪዥን የአማረኛው ክፍል ባልደረቦች ለስራ በሔዱበት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ መታሰራቸውን ትግራይ ቴሌቪዥን የአማረኛ ዝግጅት ክፍል ለአዲስ ማለዳ ተናገረ። ዝግጅት ክፍሉ ተወካይ አስተባባሪ ቴዎድሮስ አለማየሁ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት በአሶሳ ከተማ በሚካሔደው እና የፖለቲካ ፓርቲዎች የውይይት መድረክ ላይ ተገኝተው የዜና ሽፋን እንዲሰጡ ወደ ዝግጅት ክፍሉ በተላከው ግብዣ መሰረት ወደ ስፍራው በኃይሉ ውቤ እና ዳዊት ከበደ የተባሉ አንድ ሪፖርተር እና አንድ ካሜራ ባለሙያ መላካቸውን አስታውቀዋል።

አዲስ አበባ ከሚገኘው የጣቢያው ቅርንጫፍ ቢሮ ወደ አሶሳ ያመሩት ባልደረቦችም ታናንት ጥር 4/2012 ምሽት ላይ እራት ተመግበው ወደ ማደሪያቸው ሲመለሱ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ለማወቅ ተችሏል። ዜናውን አጠናቀው ሰርተው ዛሬ ጥር 5 ወደ መስሪያ ቤታቸው ተመልሰው ሪፖርት ማድረግ ቢኖርባቸውም ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ዝግጅት ክፍሉ ገልጿል።  

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here