በቀጣይ ስድስት ወራት አዲስ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ግንባታ እንደሚጀመር ተገለጸ

0
956

በተያዘው በጀት ዓመት ኹለተኛው አጋማሽ ላይ በትልቅነቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተፎካካሪ የሆነ አየር ማረፊያ ለማስገንባት ዝግጅት መጠናቀቁቀን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ። አየር መንገዱ በኦሮሚያ ክልል በቢሾፍቱ እና በዝቋላ መካከል በሚገኝ አካባቢ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ለማስገንባት ዕቅድ ይዞ ቦታ መረጣውም የተጠናቀቀ ሲሆን በቅርቡም የቦታ ርክክቡ እንደሚከናወን አስታውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ተወልደ ገብረማሪያምን ዋቢ አድርጎ ኢቢሲ እንደዘገበው የሚገነባው አዲሱ አየር ማረፊያ በፈረንሳይ  ዋና ከተማ ፓሪስ ከሚገኘው ቻርለስ ደጎል አየር ማረፊያ በትልቀቱ እንደሚልቅ ለማወቅ ተችሏል። ዋና ስራ አስፈጻሚው አያይዘውም በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የሚታየውን መጨናነቅ በሰፊው ይቀርፋል የተባለለት ይኸው አየር ማረፊያ የግንባታ ሒደቱ ይህ ዓመት ሳይጠናቀቅ በበጀት ዓመቱ ኹለተኛው አጋማሽ ላይ እንደሚጀመር ለማወቅ ተችሏል።

ከግንባታው ጋር ተያይዞም በሚነሱ የአካባቢው ማኅበረሰብ ለሚያገኙት ካሳም ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ እንደሚገኝ አየር መንገዱ አስታውቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here